am_tn/zep/01/04.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ቁጥር 1፥2-18 የያህዌን ፍርድ ያመለክታል፡፡ ቁጥር 1፥4-16 ያህዌ የይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያመጣውን ፍርድ ያመለክታል፡፡

እጄን በይሁዳ ላይ… አነሣለሁ

ይህ እግዚአብሔር እንደሚቀጣ የሚያመለክት ፈሊጥ ነው፡፡ ‹‹ይሁዳን እቀጣለሁ››

የበአልን ትሩፍ፣ የጣዖታቱንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም… በሰገነት ላይ ወጥተው የሚሰግዱትን… የሚሰግዱትንና የሚምሉትን… አጠፋለሁ

‹‹አጠፋለሁ›› የሚለው ግሥ የሚያመለከተው እነዚህን ሐረጐች ሁሉ ቢሆንም፣ ድግግሞሽን ለማስወገድ ሲባል ጥቅም ላይ የዋለው አንዴ ብቻ ነው፡፡ ‹‹የበአልን ትሩፍ፣ የጣዖታቱንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም… በሰገንት ላይ ወጥተው የሚሰግዱትን… የሚሰግዱትንና የሚምሉትን… አጠፋለሁ››

መቁረጥ

ማጥፋት አንድን ነገር ከአካሉ ቆርጦ መጣል ማለት እንደ ሆነ ተነግሮአል፡፡ ሶፎንያስ 1፥3 ላይ ይህን እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ ‹‹ማስወገድ››

የአመንዝራ ካህናቱን ስም ሁሉ ከዚህ ስፍራ አጠፋለሁ፡፡

እዚህ ላይ ስማቸውን አጠፋለሁ ሲባል ሰዎች እንዲረሷቸው አደርጋለሁ ማለት ነው፡፡ ‹‹ጣዖት የሚያመልኩትን ካህናት ሰዎች ሁሉ እንዲረሷቸው አደርጋለሁ››

በንጉሣቸው

‹‹በሚልኮምም›› ለሚለው አማራጭ ትርጒም ለማግኘት የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት፡፡

ያህዌን አልፈለጉም፤ እንዲመራቸውም አልጠየቁም

ያህዌን መፈለግ 1) ከእግዚአብሔር ርዳታ መለመን ወይም 2) ስለ እግዚአብሔር ማሰብና ለእርሱ መታዘዝን ያመለክታል፡፡ ስለ ያህዌ አላሰቡም ወይም እንዲመራቸው አልለመኑም፡፡