am_tn/zep/01/01.md

2.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡- የመጣው የያህዌ ቃል

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ከእግዚአብሔር የመጣ ጠቃሚ መልእክት ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ መልእክት ሰጠ›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ይህን መልእክት ተናገረ››

ያህዌ

ይህ በብሉይ ኪዳን ዘመን ለሕዝቡ የገለጠው የእግዚብሔር ስም ነው፡፡ ይህን እንዴት እንደምትተረጉም፤ ስለ ያህዌ ከቃላት ትርጒም ገጽ ተመልከት፡፡

የጐዶልያስ ልጅ፤ የአማርያ ልጅ፤ የሕዝቅያስ ልጅ

ይህ የሶፎንያስ ዘሮች ዝርዝር ነው፡፡ ይህ ‹‹የ… ልጅ›› የሚለው ሐረግ ሰፋ ባለ መልኩ፣ ‹‹…ትውልድ›› ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹ሕዝቅያስ›› የሚለው ንጉሥ ሕዝቅያስን ያመለክታል፡፡ ይህን በጣም ግልጽ ማድረግ ይቻላል፤ ‹‹ከሕዝቅያስ የተወለደው የአማርያ የልጅ ልጅ ልጅ የጐዶልያስ ልጅ፡፡››

ማንኛውንም ነገር ከምድር ላይ አጠፋለሁ… ሰውን ከምድር ገጽ በማስወግድበት ጊዜ

‹‹ማንኛውም ነገር›› እና ‹‹ሰውን ከምድር በማስወግድበት ጊዜ›› የተሰኙ ቃሎች ምን ያህል በሰዎች ኀጢአት መቆጣቱን ለማሳየት ሆን ብሎ ያህዌ የተጠቀመባቸው ናቸው፡፡ ያህዌ ንስሐ የማያደርጉ ኀጢአተኞችንና ሕይወት ያላቸው ነገሮችን ሁሉ ያጠፋል፡፡

ከምድረ ገጽ ማንኛውንም ነገር ማጥፋት

‹‹በመላው ምድር ላይ ያለውን ማንኛውንም ነገር ማጥፋት››

ይህ የያህዌ ቃል ነው

የተናገረው በእርግጥ መሆኑን ለማመልከት ያህዌ ስሙን በማንሣት ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ‹‹ያህዌ እንዲህ አለ›› ወይም፣ ‹‹እኔ ያህዌ ይህን ተናግሬአለሁ፡፡››

ሰውንና እንስሳን

‹‹ሕዝብንና እንስሳን››

ማጥፋት

ተቃራራቢ ትርጉሙ 1) ከፍርዱ በኃላ የሚቀረውን የፍርስራሽ ክምር ወይም 2) ያህዌ የሚያጠፋቸው ጣዖቶችን ሊያመለክት ችላል፡፡

መቁረጥ

ስለ ማጥፋት ሲናገር አንድ ነገር ከአካሉ ቆርጦ ስለ መጣል ይናገራል፡፡ ‹‹ማስወገድ››