am_tn/zec/14/16.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ጥቅሶች ኢየሩሳሌምን ለመያዝ የሚደረገውን የመጨረሻ ጦርነትና እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያድናት መግለጽ ይቀጥላሉ፡፡

በኢየሩሳሌም ላይ ከመጡት

“በ … ላይ መጡ” የሚለው ፈሊጣዊ አባባል ነው፡፡ አት. “ኢየሩሳሌምን ያጠቁት” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያ ይልቅ ከዓመት ወደ ዓመት ይወጣሉ

ከዚያ ይልቅ ወደ ኢየሩሳሌም በየዓመቱ ይወጣሉ፡፡

የመጠለያዎች በዓል

‘የማረፊያ ቦታዎች በዓል’ ወይም ‘የዳሶች በዓል’ ወይም ‘የድንኳኖች በዓል’

ከያህዌ ዘንድ የሆነ ቸነፈር መንግሥታትን ያጠቃል

አንድን ሕዝብ በቸነፈር እንዲሰቃይ ማድረግ ቸነፈሩ እንደ ሠራዊት ሕዝቡን እንደሚያጠቃው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አት. “በመንግሥታት ሕዝቦች መካከል ያህዌ ቸነፈር እንዲመጣ ያደርጋል፡፡” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)