am_tn/zec/14/12.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ጥቅሶች ኢየሩሳሌምን ለመያዝ የሚደረገውን የመጨረሻ ጦርነትና እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያድናት መግለጽ ይቀጥላሉ፡፡

ገና በእግሮቻቸው ቆመው ሳሉ

“ቆመው ሳሉ” ይህ ሥጋቸው ምን ያህል ፈጥኖ እንደሚበሰብስ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ ለመተኛት እንኳን ጊዜ አይኖራቸውም፡፡

በመካከላቸውም ከያህዌ ዘንድ ያ ታላቅ ፍርሃት ይመጣባቸዋል

‘ፍርሃት’ የሚለው የነገር ስም ‘ድንጋጤ’ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት. “ያህዌ ሕዝቡ በጣም እንዲደነግጡ ያደርጋቸዋል” (የነገር ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የአንዱ እጅ የሌላውን እጅ ይይዛል፣ የአንደኛውም እጅ በሌላው እጅ ላይ ይነሳል

እነዚህ ፈሊጣዊ አባባሎች በሌላው ሰው ላይ በጠላትነት መነሳትን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ አት. “እያንዳንዱ ሰው ሌላውን ሰው ይይዘዋል፣ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፡፡” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)