am_tn/zec/14/06.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ጥቅሶች ኢየሩሳሌምን ለመያዝ የሚደረገውን የመጨረሻ ጦርነትና እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያድናት መግለጽ ይቀጥላሉ፡፡

በዚያን ቀን

“በዚያን ወቅት”

ብርሃን አይኖርም

በግንዛቤ በተገኘው መረጃ መሠረት ከፀሐይ የሚገኝ ብርሃን አይኖርም፡፡ አት. “የፀሐይ ብርሃን አይኖርም” (ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ያህዌ ዘንድ ብቻ የታወቀ ቀን

ይህ በተናጋሪ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት. “ያ ቀን መቼ እንደሚጀምር የሚያውቀው ያህዌ ብቻ ነው፡፡” ወይም “ያህዌ ብቻ ያ ቀን መቼ እንደሚጀምር ያውቃል፡፡” (ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚለውን ይመልከቱ)

የሕይወት ውሃ

ይህ በመደበኛነት በአንድ ቦታ የረጋ ወይም ጮሮቃ ውሃ ሳይሆን ወረጅ ወይም ፈሳሽ ውሃ ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

የምሥራቅ ባሕር

ይህ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ያለውን ሙት-ባሕርን ያመለክታል፡፡

የምዕራብ ባሕር

ይህ ሜዴትራኒያን ባሕርን (ታላቁን ባሕር) ያመለክታል፡፡