am_tn/zec/14/05.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ጥቅሶች ኢየሩሳሌምን ለመያዝ የሚደረገውን የመጨረሻ ጦርነትና እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያድናት መግለጽ ይቀጥላሉ፡፡

እናንተ ትሸሻላችሁ

እዚህ ላይ ‘እናንተ’ የሚለው የብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተውም የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ነው፡፡ (አንተ እና እናንተ የሚገለጽባቸው መልኮች የሚለውን ይመልከቱ)

በእግዚአብሔር ተራሮች መካከል

ይህ የኢየሩሳሌም ተራራ ለሁለት ከተከፈለ በኋላ የሚፈጠሩትን ተራራዎች ይመለከታል፡፡

አጼል

ይህ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ ከተማ ወይም መንደር ስም ነው፡፡ (ስምን እንዴት መተርጎም እንደሚገባ የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚህ ቀደም እንደሸሻችሁ ትሸሻላችሁ

እዚህ ላይ ‘ትሸሻላችሁ’ በሚለው በውስጠ ታዋቂ ‘እናንተ’ የሚለው የሚያመለክተው የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ነው፡፡ ነገር ግን ‘እንደሸሻችሁ’ የሚለው የሚያመለክተው ከብዙ ዓመታት በፊት የተፈጸመ ድርጊትን በመሆኑ የሸሹት ቀደምት አባታቶቻቸው ናቸው፡፡ አት. “ቀደምት አባቶቻችሁ እንደሸሹ ትሸሻላችሁ” (ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን

እዚህ ላይ ‘በ … ዘመን’ የሚለው ፈሊጣዊ አባባል ሲሆን ዖዝያን ንጉሥ በነበረበት ጊዜ ማለት ነው፡፡ አት. “ዖዝያን ንጉሥ በነበረበት ጊዜ” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ቅዱሳኑም

ይህ ምናልባት የእግዚአብሔርን መላእክት የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም፡፡