am_tn/zec/14/03.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ጥቅሶች ኢየሩሳሌምን ለመያዝ የሚደረገውን የመጨረሻ ጦርነትና እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያድናት መግለጽ ይቀጥላሉ፡፡ ያህዌ እንደሚመጣና እንደሚዋጋ ተዋጊ ተደርጎ ተገልጾአል፡፡

በጦርነት ጊዜ እንደሚዋጋ

“በቀደሙት ጊዜያት በጦርነት ሲዋጋ እንደነበረ”

በዚያን ቀን

“በዚያን ወቅት”

እግሮቹ በኢየሩሳሌም ተራራ ላይ ይቆማሉ

እዚህ ላይ ‘እግሮቹ’ የሚለው ያህዌን ይወክላል፡፡ አት. “በኢየሩሳሌም ተራራ ላይ ይቆማል፡፡” (በክፋይ የተወከለ አካል የሚለውን ይመልከቱ)

የኢየሩሳሌም ተራራም ተከፍሎ … ታላቅ ሸለቆ ይሆናል

ይህ በተናጋሪ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት. “የያህዌ ሕላዌ የኢየሩሳሌምን ተራራ ሁለት ቦታ ከፍሎ ታላቅ ሸለቆ በዚያ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡” (ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚለውን ይመልከቱ)