am_tn/zec/14/01.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይሀ ምዕራፍ ኢየሩሳሌምን ለመያዝ የሚደረገውን የመጨረሻ ጦርነትና እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያድናት ይገልጻል፡፡

ብዝበዛችሁ በመካከላችሁ የሚከፋፈልበት የያህዌ ቀን ይመጣል

ወደፊት የሚመጣ ጊዜ ‘ቀን እንደሚመጣ’ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ‘የሚከፋፈልበት’ የሚለው ቃል በተናጋሪ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት. “ያህዌ ፈጥኖ ይፈርድባችኋል፣ ጠላቶቻችሁም ንብረቶቻችሁን ሁሉ እንዲወስዱና ዓይኖቻችሁ እያዩ ለራሳቸው እንዲከፋፈሉት ይፈቅድላቸዋል፡፡” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚሉትን ይመልከቱ)

ሁሉንም መንግሥታት በኢየሩሳሌም ላይ ለጦርነት እሰበስባቸዋለሁ

እዚህ ላይ ‘ሁሉንም መንግሥታት’ የሚለው ብዙ መንግሥታት ለማለት የማጠቃለል አባባል ነው፡፡ አት. “ብዙ መንግሥታት ኢየሩሳሌምን እንዲያጠቋት አደርጋለሁ፡፡” (ግነት እና የማጠቃለል አባባል የሚሉትን ይመልከቱ)

ከተማይቱ ትያዛለች

ይህ በተናጋሪ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት. “ጠላቶቻችሁ ከተማይቱን ይይዟታል፡፡” (ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤቶች ይበዘበዛሉ፣ ሴቶችም ይደፈራሉ

ይህ በተናጋሪ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት. “ጠላቶች ቤቶችን ይበዘብዛሉ፣ ሴቶችንም ይደፍራሉ፡፡” (ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚለውን ይመልከቱ)

የሚቀረው ሕዝብ ከከተማይቱ አይወገድም

ሕዝቡን ከከተማይቱ አለመውሰድ ሕዝቡ ‘እንደማይወገድ’ ተደርገ ተነግሯል፡፡ ይህ በተናጋሪ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት. “ጠላቶቻችሁ ቀሪው ሕዝብ በከተማይቱ እንዲቆይ ይፈቅዱለታል፡፡” (ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚለውን ይመልከቱ)