am_tn/zec/12/07.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ጥቅሶች በኢየሩሳሌም ላይ ሊመጣ ያለውን ጥቃትና እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያድናቸው መናገር ይቃጥላሉ፡፡

የይሁዳ ድንኳኖች

እዚህ ላይ ‘ድንኳኖች’ ቤቶችን ይወክላሉ፣ ቤቶች ደግሞ በውስጣቸው የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላሉ፡፡ አት. “የይሁዳ ሕዝብ” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

የዳዊት ቤት

ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፡ - 1)የዳዊት ዝርያዎች ወይም 2)የሕዝቡ የገዢ መደብ (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል

ይህ ምስስሎሽ ደካሞች የሆኑት ጠንካሮች ይሆናሉ የሚል ትርጉም አለው፡፡ አት. “ደካሞች የሆኑት እንደ ዳዊት ብርቱዎች ይሆናሉ” (ምስስሎሽ የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌ መልአክ

ይህ ሕዝቡን እንዲጠብቅ በያህዌ የተላከ መልአክ ነው፡፡