am_tn/zec/12/06.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ጥቅሶች በኢየሩሳሌም ላይ ሊመጣ ያለውን ጥቃትና እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያድናቸው መናገር ይቃጥላሉ፡፡

በእንጨት መካከል እንዳለ የእሳት ምድጃ … በነዶም መካከል

ይህ ምስስሎሽ ያህዌ የይሁዳን መሪዎች ጠንካሮች እንዲሆኑና ሕዝባቸውም ጠላቶቻቸውን ድል ወደ ማድረግ እንዲመሩ ያስችላቸዋል ማለት ነው፡፡ አት. “በተከመሪ እንጨት መካከል እንደ እሳት ምድጃ … በእርሻ ውስጥ የቆመ ያልታጨደ ነዶ” (ምስስሎሽ የሚለውን ይመልከቱ)

የእሳት ምድጃ

የጥንት ሰዎች የሚነድ ከሰልን ይዘው የሚሄዱባቸው የሸክላ ማሰሮዎች

የፋና ነበልባል

በአንድ ጫፍ በኩል የሚነድና አንድ ሰው በሚጓዝበት ጊዜ ብርሃን የሚሰጥ ወይም እሳትን አንድ ሌላ ስፍራ የሚያደርስ

በዙሪያው ያሉትን ሰዎች ይበላል

ሰዎቹን ፈጽሞ መደምሰስ የይሁዳ ሰዎች ሰዎቹን እንደሚበሏቸው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አት. “የአካባቢውን ሕዝቦች ያጠፋሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በቀኛቸውና በግራቸው

እዚህ ላይ ‘ቀኝ’ እና ‘ግራ’ የሚለው በሁሉም አቅጣጫ የሚለውን ይወክላል፡፡ አት. “በሁሉም አቅጣጫ” (… የሚለውን ይመልከቱ)

ኢየሩሳሌም በድጋሚ በስፍራዋ ትቀመጣለች

እዚህ ላይ ‘ኢየሩሳሌም’ በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላል፡፡ አት. “የኢየሩሳሌም ሕዝቦች እንደገና በራሳቸው ከተማ ይኖራሉ” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)