am_tn/zec/12/01.md

2.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ጥቅሶች በኢየሩሳሌም ላይ ሊመጣ ያለውን ጥቃትና እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያድናቸው የሚናገረውን ክፍል ይጀምራል፡፡

ይህ እስራኤልን በሚመለከት የያህዌ ቃል እወጃ ነው

“ይህ እስራኤልን በሚመለከት ያህዌ ያወጀው መልእክት ነው”

ሰማያትን የዘረጋ

ይህ ሰማይ እንደ ብራና የተጠቀለለና መዘርጋት እንደሚያስፈልገው የሚናገር ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አት. “ሰማይን የፈጠረ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የምድርን መሠረት ያስቀመጠ

ይህ ምድርን መሠረት እንዳለው ሕንፃ አድርጎ የሚናገር ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አት. “ምድርን በሞላ በስፍራው የሚያስቀምጥ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰው ውስጥ የሰውን ልጅ መንፈስ የቀረጸ

ይህ መንፈስን ሸክላ ሠሪ እንደሚቀርጸው ሸክላ አድርጎ የሚናገር ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አት. “የሰውን ልጅ መንፈስ የሚፈጥር”

ኢየሩሳሌምን የሚያንገዳግድ ጽዋ አደርጋታለሁ

ያህዌ ኢየሩሳሌምን ለመቅጣት እንደሚጠብቃት ማድረጉን ኢየሩሳሌምን የአልኮል መጠጥ እንደሚያደርጋትና በአካባቢው ያሉት ሕዝቦች ጠጥተዋት እንደሚንገዳገዱ አድርጎ እየተናገረ ነው፡፡ አት. “በቅርቡ ኢየሩሳሌምን የምታንገዳግድ ጽዋ እንደማደርጋት ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ጽዋነት

እዚህ ላይ ‘ጽዋ’ ጽዋውንና በጽዋ ውስጥ ያለውን ይወክላል፡፡ አት. “በወይን ጠጅ ወደተሞላ ጽዋነት” ወይም “በአልኮል መጠጥ እንደተሞላ ጽዋ” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሷን የከበቧት

እዚህ ላይ ‘እርሷን’ የሚለው የሚያመለክተው ኢየሩሳሌምን ነው፡፡ በዕብራውያን ዘንድ አንድ አገር ወይም አንድን ከተማ ሴት እንደሆነች አድርጎ መናገር የተለመደ ነው፡፡ (ሰውኛ የሚለውን ይመልከቱ)

ኢየሩሳሌምን ለሕዝቦች ሁሉ ከባድ ዐለት አደርጋታለሁ

ያህዌ ኢየሩሳሌምን የአካባቢውን ሕዝቦች ለመቅጫ መጠቀሙ ኢየሩሳሌምን ከባድ ዐለት እንደሚያደርጋት ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አት. “ኢየሩሳሌምን ለሕዝቦች ከባድ ዐለት እንደማደርጋት ያለ ይሆናል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)