am_tn/zec/11/17.md

1.1 KiB

ሰይፍ

እዚህ ላይ ‘ሰይፍ’ ሕዝቡን የሚያጠቁትን ጠላቶች ይወክላል፡፡ አት. “ጠላቶች” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

በክንዱና በቀኝ ዓይኑ ላይ ይምጡበት

እዚህ ላይ ‘ይምጡበት’ የሚለው ፈሊጣዊ አባባል ነው፡፡ አት. “ቀኝ ክንዱን ያቁስሉት ደግሞም ቀኝ ዓይኑን ይውጉት” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ክንዱ

የእርሱ ‘ክንድ’ የመዋጋት ኃይሉን ይወክላል፡፡ (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀኝ ዓይኑ

አንድ ወታደር ቀኝ ዓይኑን በግራ እጁ በያዘው ጋሻ ዙሪያ ያለውን ለማየት ይጠቀምበታል፡፡ ቀኝ ዓይኑ ከቆሰለ በጦርነት ጊዜ ለመዋጋት መመልከት አይችልም፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ክንዱ ትስለል

“ክንዱ ትበስብስ” ወይም “ክንዱ ፈጽማ ከጥቅም ውጪ ትሁን”