am_tn/zec/11/15.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ በዘካርያስ 11፡4 ስለ ሁለቱ እረኞች የተጀመረውን ታሪክ ይቀጥላል፡፡ ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፡ - 1) ያህዌ ሕዝቡን እንዴት እንደሚይዝ ለመግለጽ በተምሳሌታዊ ተግባር ዘካርያስ የአንድ መንጋ እረኛ ይሆናል፡፡ 2)ያህዌ ሕዝቡን እንዴት እንደሚይዝ ለማስተማር ዘካርያስ ምሳሌ ይናገራል፡፡ ከእነዚህ ሁለት ትርጉሞች የትኛው ትክክል እንደሆነ እርግጠኛ ስላልሆነ፣ በትርጉም ወቅት ማንኛውንም ትርጉም አለመወሰን መልካም ይሆናል፡፡ (ተምሳሌታዊ ተግባር እና ምሳሌዎች የሚሉትን ይመልከቱ)

አንድን እረኛ በቦታው ላስቀምጥ ነው

እዚህ ላይ ‘በቦታው ማስቀመጥ’ ፈሊጣዊ አባባል ነው፡፡ አት. “በምድሪቱ እረኛን ልሾም ነው” ወይም “ኃላፊነት ያለውን እረኛ በምድሪቱ ላስቀምጥ ነው፡፡” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

የሰባውን በግ

‘እጅግ የሰባውን በግ’ ወይም ‘ምርጥ የሆነውን በግ’

ሰኮናቸውን ይቀለጣጥማል

ይህ ምናልባት በክፋት የሚፈጸም ድርጊት ሳይሆን አይቀርም፡፡