am_tn/zec/11/13.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ስለ እረኞችን ስለ በጎች የሚነገረው ምሳሌ ቀጥሏል፡፡

ግምጃ ቤት

ይህ በያህዌ ቤተ መቅደስ ካህናቱ ገንዘብ የሚያስቀምጡበት ቦታ ነው፡፡ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህንን ‘አንጥረኛ’ ብለው ይተረጉሙታል፡፡ ይሄ ሰው (አንጥረኛው) ዕቃዎችን (ድስቶችን፣ ማንቆርቆሪያዎችን) ለመሥራት ብረታ ብረትን የሚያቀልጥ ሰው ነው፡፡ እዚህ ላይ ያህዌ ክፍያው እጅግ ዝቅ ያለ በመሆኑ እረኛው ምን ያህል እንደተዋረደ ለመግለጽ ብሩን ያቀልጠዋል ማለት ፈልጎ ነው፡፡

በጣም ጥሩ ዋጋ

የያህዌን ሥራ ለሚሠራ ይህ በጣም ዝቅተኛ ክፍያ ለመሆኑ እዚህ ላይ ያህዌ የሽሙጥ አነጋገር እየተጠቀመ ነው፡፡ አት. “ከሞኝነት የሚቆጠር እጅግ ዝቅ ያለ ገንዘብ” (ሽሙጥ የሚለውን ይመልከቱ)

በይሁዳና በእስራኤል መካከል

እዚህ ላይ ‘ይሁዳ’ በደቡባዊው መንግሥት የነበረው ሕዝብ፣ ‘እስራኤል’ ደግሞ በሰሜናዊው መንግሥት የነበረውን ሕዝብ ይወክላሉ፡፡ አት. “በይሁዳ ሕዝብና በእስራኤል ሕዝብ መካከል” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)