am_tn/zec/11/04.md

2.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በ11፡4-17 የሁለት እረኞች ታሪክ ቀርቧል፡፡ ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፡ -1)ያህዌ ሕዝቡን እንዴት እንደሚይዝ ለመግለጽ በተምሳሌታዊ ተግባር ዘካርያስ የአንድ መንጋ እረኛ ይሆናል፡፡ 2)ያህዌ ሕዝቡን እንዴት እንደሚይዝ ለማስተማር ዘካርያስ ምሳሌ ይናገራል፡፡ ከእነዚህ ሁለት ትርጉሞች የትኛው ትክክል እንደሆነ እርግጠኛ ስላልሆነ፣ በትርጉም ወቅት ማንኛውንም ትርጉም አለመወሰን መልካም ይሆናል፡፡ (ተምሳሌታዊ ተግባር እና ምሳሌዎች የሚሉትን ይመልከቱ)

ለዕርድ የተለዩትን መንጋዎች ጠብቅ

“ባላቤቶቻቸው ለዕርድ ያቀዷቸውን በጎች ተንከባከብ”

አልተቀጡም

ይህ በተናጋሪ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት. “ማንም አይቀጣቸውም” (ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚለውን ይመልከቱ)

የምድሪቱ ነዋሪዎች

“የምድሩ ሕዝብ”

ያህዌ … እንዲህ ይላል

እያወጀ ያለውን ነገር እርግጠኛነት ለመግለጽ ያህዌ ስለ ራሱ ስሙን በመጥቀስ ይናገራል፡፡ በዘካርያስ 1፡4 ላይ ተመሳሳይ የሆነውን ሐረግ እንዴት እንደተረጎማችሁት ዞር ብላችሁ ተመልከቱ፡፡ አት. “የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንደዚህ ብሎ ተናግሯል” ወይም “እኔ የሠራዊት ጌታ ያህዌ የምናገረው ይህንን ነው” (‘መጀመሪያ፣ ሁለተኛ፣ ሶስተኛ ሰው’ የሚለውን ይመልከቱ)

ተመልከቱ

“አድምጡ” ወይም “ልብ አድርጉ”

እኔ ራሴ

‘ራሴ’ የሚለው ቃል እነዚህን ነገሮች የሚያደርገው ይህዌ እንደሆነ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ (አጽንዖት የሚሰጡ ተወላጠ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ሰውን ሁሉ ለባልንጀራው እጅና ለንጉሡ እጅ አሳልፎ መስጠት

እዚህ ላይ ‘እጅ’ ኃይልን ወይም መቆጣጠርን ይወክላል፡፡ አት. “ሕዝቡ እርስ በርሳቸው እንዲጎዳዱ አደርጋለሁ፣ ንጉሡም ይጨቁናቸዋል፡፡” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

ማናቸውንም ከእጃቸው አላድናቸውም

እዚህ ላይ ‘እጅ’ ኃይልን ወይም መቆጣጠርን ይወክላል፡፡ አት. “ከሚጎዷቸው አላድናቸውም” ወይም “አላድናቸውም” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)