am_tn/zec/11/01.md

3.2 KiB

ሊባኖስ ሆይ፣ እሳት እንዲያወድማቸው በሮችሽን ክፈቺ

ሊሆን ያለውን መቋቋም አለመቻሉ ሊባኖስ በሮችዋን እንደምትከፍት ሆኖ እየተነገረ ነው፡፡ እዚህ ላይ ‘ሊባኖስ’ የሊባኖስን ሕዝብ የሚወክል ስመ-መስል ስያሜ ነው፡፡ አት. “የሊባኖስ ሕዝብ ሆይ፣ እሳት ሊያወድም ስለሆነ ተዘጋጁ” ወይም “የሊባኖስ ሕዝብ ሊያወድም ያለውን እሳት ለማስቆም አትሞክሩ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ስመ-ምስል ስያሜ የሚሉትን ይመልከቱ)

እሳት ዝግባዎችሽን እንዲያወድም

እሳት ዝግባዎችን ፈጽሞ ማቃጠሉ እሳት ዝግባዎቹን እንደሚያወድም ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አት. “እሳት ሙሉ በሙሉ ዝግባዎችሽን እንዲያወድም” ወይም “እሳት ሙሉ በሙሉ ዝግባዎችሽን እንዲያቃጥል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የጥድ ዛፎች ሆይ፣ የዝግባ ዛፎች ወድቀዋልና አልቅሱ

የጥድ ዛፎች እንደ ሰው እንደሚያዝኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አት. “ዛፎች ሰዎች ቢሆኑ ኖሮ በኃዘን ያለቅሱ ነበር፡፡ ዝግባዎቹ ስለተቃጠሉና ስለወደቁ የጥድ ዛፎቹ ለብቻቸው ቆመዋል፡፡” (ሰውኛ የሚለውን ይመልከቱ)

የከበሩትም ጠፍተዋል

ይህ በተናጋሪ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት. “ግርማ ያላቸው የዝግባ ዛፎች ከእንግዲህ የሉም” ወይም “የዝግባ ዛፎቹ በአንድ ወቅት ግርማ ያላቸው ነበሩ፣ አሁን ግን ጠፍተዋል፡፡” (ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚለውን ይመልከቱ)

የባሳን ወርካዎች ሆይ፣ አልቅሱ፣ ጠንካራ የነበረው ደን ጠፍቶአልና

የባሳን ወርካዎች እንደ ሰው እንደሚያዝኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አት. “ጥቅጥቅ ያሉት ደኖቻቸው ስለተመነጠሩ፣ የባሳን ወርካዎች ሰዎች ቢሆኑ ኖሮ ያለቅሱ ነበር፡፡” (ሰውኛ የሚለውን ይመልከቱ)

እረኞች ዋይ ይላሉ

“እረኞች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያለቅሳሉ”

ክብራቸው ተገፎአልና

እዚህ ላይ ‘ክብራቸው’ የሚለው ምናልባት እረኞች በጎቻቸውን የሚያሰማሩባቸውን ለምለም ግጦሽ የሚወክል ሳይሆን አይቀርም፡፡ አት. “ለምለም ግጦሾቻቸው ጠፍተዋልና” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

የዮርዳኖስ ወንዝ ትዕቢት ወድሟል

እዚህ ላይ ‘ትዕቢት’ ምናልባት የሚለው በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ የበቀሉትን ደኖች የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም፡፡ አት. “ይኖሩባቸው በነበሩት በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ የነበሩት ዛፎችና ቁጥቋጦዎች ስለወደሙ” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)