am_tn/zec/10/11.md

3.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከቁ.6-12 ላይ ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ ይናገራል፡፡

በእነርሱ የመከራ ባሕር ውስጥ አልፋለሁ

የእግዚአብሔር ቃል ብዙውን ጊዜ ባሕር የብዙ ችግሮችና ጭንቀቶች ምስል እንደሆነ ያመለክታል፡፡ እዚህ ላይ ያህዌ በእነዚህ ጭንቀቶች ውስጥ ሲያልፉ ሕዝቡን እንደሚያጅባቸው እየተናገረ ነው፡፡ አት. “እኔ ከእነርሱ ጋር እሄዳለሁ፣ በብዙ ጭንቀቶቻቸው ውስጥ በሚያልፉበትም ጊዜ እረዳቸዋለሁ፡፡” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የዚያንም ባሕር ማዕበል እመታለሁ

እዚህ ላይ የባሕሩን ማዕበል ‘እመታለሁ’ የሚለው ማዕበሉ እንዳይከሰት አስቆመዋለሁ ለማለት የሚውል ፈሊጣዊ አባባል ነው፡፡ የሕዝቡን ጭንቀት ማስቆም የዚያን ባሕር ማዕበል እንደማረጋጋት ሆኖ እየተነገረ ነው፡፡ አት. “ያንን የመከራ ባሕር ማዕበል እንዲቆም አደርገዋለሁ” (ፈሊጣዊ አባባል እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

የዓባይም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል

“የዓባይ ወንዝ ውሃውን ሁሉ እንዲያጣ አደርገዋለሁ”

የአሦርም ግርማ ይዋረዳል

እዚህ ላይ ‘የአሦር ግርማ’ የአሦርን ጦር ሠራዊት የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም፡፡ (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

የግብፅም በትረ መንግሥት ከግብፃውያን ይወገዳል

እዚሀ ላይ ‘የግብፅ በትረ መንግሥት’ የግብፅን ፖለቲካዊ ኃይል የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም፡፡ አት. “ግብፅ ሌሎች አገሮችን የመግዛት ኃይሏ ያበቃል” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

በእኔ በራሴ አበረታቸዋለሁ

“ብርቱ እንዲሆኑና በእኔ እንዲያምኑ አደርጋቸዋለሁ”

በስሜም ይመላለሳሉ

እዚህ ላይ ‘በስሜ’ የሚለው ያህዌ የሚለውን ያደርጋሉ የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ አባባል ነው፡፡ አት. “እኔ እንዲያደርጉ እንደምፈልግባቸው ይታዘዙኛል ያከብሩኛልም፡፡” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ያህዌ … እንዲህ ይላል

እያወጀ ያለውን ነገር እርግጠኛነት ለመግለጽ ያህዌ ስለ ራሱ ስሙን በመጥቀስ ይናገራል፡፡ በዘካርያስ 1፡4 ላይ ተመሳሳይ የሆነውን ሐረግ እንዴት እንደተረጎማችሁት ዞር ብላችሁ ተመልከቱ፡፡ አት. “የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንደዚህ ብሎ ተናግሯል” ወይም “እኔ የሠራዊት ጌታ ያህዌ የምናገረው ይህንን ነው” (‘መጀመሪያ፣ ሁለተኛ፣ ሶስተኛ ሰው’ የሚለውን ይመልከቱ)