am_tn/zec/10/06.md

2.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከቁ.6-12 ላይ ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ ይናገራል፡፡

የይሁዳ ቤት

‘ቤት’ የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ስመ-ምስል ስያሜ ነው፡፡ እዚህ ላይ የሚያመለክተው የይሁዳንና የቢንያምን ዝርያዎች የሚያካትተውን የእስራኤልን መንግሥት ነው፡፡ አት. “ይሁዳ” ወይም “የይሁዳ መንግሥት” ወይም “የይሁዳ ሕዝብ” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

የዮሴፍ ቤት

‘ቤት’ የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ስመ-ምስል ስያሜ ነው፡፡ እዚህ ላይ የሚያመለክተው የይሁዳንና የቢንያምን ዝርያዎች የሚያካትተውን የይሁዳን መንግሥት ነው፡፡ አት. “እስራኤል” ወይም “የእስራኤል መንግሥት” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

አልጣልኳቸውም

ይህ ስለ ሕዝቡ ያህዌ እንደሚያወልቀውና እንደሚጥለው እንደተቀዳደ ወይም እንደ ቆሸሸ ልብስ ይናገራል፡፡ ይህ መተውን ወይም መጣልን በተምሳሌትነት ይገልጻል፡፡ አት. “አልጣልኳቸውም” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ተምሳሌታዊ ተግባር የሚሉትን ይመልከቱ)

ኤፍሬም እንደ ተዋጊ ይሆናል

‘ኤፍሬም’ እዚህ ላይ ሰሜናዊውን የእስራኤል መንግሥት ያመለክታል፡፡ ተዋጊዎች ብርቱዎች ናቸው፡፡ አት. “ኤፍሬም እጅግ ብርቱ ይሆናል” (ምስስሎሽ የሚለውን ይመልከቱ)

የወይን ጠጅ የጠጡ ደስ እንደሚላቸው ልባቸው ሐሴት ያደርጋል

እዚህ ላይ ‘ልብ’ መላውን ሰው ያመለክታል፡፡ ወይን ጠጅ በመጠጣት ደስ እንደሚለው ሁሉ እነርሱም እንደዚሁ ደስ ይላቸዋል፡፡ አት. “በጣም ደስ ይላቸዋል” (በከፊል የተወከለ አካል እና ምስስሎሽ የሚሉትን ይመልከቱ)

ልጆቻቸው ይመለከታሉ ሐሴትም ያደርጋሉ … በእኔም ደስ ይላቸዋል

“ለእነርሱ ያህዌ ስላደረገላቸው ነገር ልጆቻቸው የተደረገውን ተመልክተው ደስ ይላቸዋል!”