am_tn/zec/10/04.md

3.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከቄ.3-5 የሚናገረው ያህዌ ይሁን ወይም ዘካርያስ በያህዌ ምትክ ሆኖ እየተናገረ እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡

ከይሁዳ የማዕዘን ራስ ድንጋይ ይመጣል

“የማዕዘኑ ራስ ድንጋይ ከይሁዳ ይመጣል” በጣም አስፈላጊ የሆነው ገዢ የሕንፃው ዋና መሠረት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አት. “ከይሁዳ ዝርያዎች አንዱ በጣም አስፈላጊ የሆነው ገዢ ይሆናል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የማዕዘን ራስ ድንጋይ … የድንኳን ካስማ … የውጊያ ቀስት

ለእነዚህ ሶስት ነገሮች ትርጉሞች ሊሆኑ የሚችሉት፡ - 1) ከይሁዳ ነገድ የሚመጣውን መሲሑን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋሉ ተምሳሌታዊ አባባሎች ሊሆኑ ይችላሉ፣ ወይም 2) ከይሁዳ የሚመጡ የተለያዩ መሪዎችን ሊያመለክት ይችላል፡፡ (ተምሳሌታዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ከእርሱም የድንኳን ካስማ

“ከእርሱ ዘንድ የድንኳን ካስማ ይመጣል” የድንኳን ካስማ ሰዎች የሚኖሩባቸውን ድንኳኖች የሚደግፉትን ገመዶች የሚይዘው ነው፡፡ እዚህ ላይ በጣም አስፈላጊ የሆነው ገዢ ድንኳኑን በስፍራው እንደሚይዘው የድንኳኑ ዋና ካስማ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አት. “አገሪቱን በአንድነት አስተባብሮ የሚይዘው መሪ ከይሁዳ ይመጣል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእርሱ ዘንድ የጦርነቱ ቀስት ይመጣል

“የጦርነቱ ቀስት ከእርሱ ዘንድ ይመጣል” እዚህ ላይ በጣም አስፈላጊ የሆነው ገዢ በጦርነት ጊዜ ጥቅም ላይ እንደሚውለው የጦርነት ቀስት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አት. “ወታደራዊው መሪ ከይሁዳ ይመጣል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእርሱ ዘንድ ማናቸውም መሪዎች በአንድነት ይመጣሉ

“ማንኛውም መሪ ከይሁዳ ይመጣል”

እንደ ተዋጊዎች ይሆናሉ … በውጊያ ወቅት ያሉ መንገዶች

ከይሁዳ የሚመጡት ገዢዎች ድል አድራጊ ተዋጊዎች እንደሆኑ ተደርገው ተነግርዋል፡፡ አት. “በጦርነት ኃይለኞች ይሆናሉ፣ ጠላቶቻቸውንም እንደ መንገድ ጭቃ ይረግጣሉ” (ምስስሎሽ የሚለውን ይመልከቱ)

በጦርነት ጊዜ ጠላቶቻቸውን እንደ መንገድ ጭቃ ይረግጣሉ

እንደ ጭቃ መርገጥ ሙሉ በሙሉ ድል ነሷቸው ለማለት የዋለ ፈሊጣዊ አባባል ነው፡፡ አት. “ጠላቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ ድል የሚያደርጉ” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ያህዌ ከእነርሱ ጋር ነው

እዚህ ላይ ‘ከእነርሱ ጋር’ የሚለው ሊረዳቸው በዚያ እንደሚገኝ የሚገልጽ ፈሊጣዊ አባባል ነው፡፡ አት. “ያህዌ ይረዳቸዋል” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

የጦር ፈረሶችን የሚጋልቡትን ያሳፍራሉ

እዚህ ላይ ኃፍረት መሸነፍን የሚያጅብና የሚወክል ነው፡፡ አት. “የጦር ፈረሶችን የሚጋልቡትን ድል ያደርጋሉ” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)