am_tn/zec/10/03.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከቄ.3-5 የሚናገረው ያህዌ ይሁን ወይም ዘካርያስ በያህዌ ምትክ ሆኖ እየተናገረ እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡

ቁጣዬ በእረኞች ላይ ነዶአል

እዚህ ላይ “እረኞች” የእግዚአብሔርን ሕዝብ መሪዎች ይወክላል፡፡ የያህዌ የቁጣ ብርታት የሚነድ እሳት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አት. “በሕዝቤ እረኞች ላይ ያለኝ ቁጣ እንደ እሳት ብርቱ ነው፡፡” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የምቀጣው ተባዕት ፍየሎችን፣ መሪዎችን ነው

ተባዕት ፍየሎች ከእንስቶቹ ይልቅ በኃይለኝነታቸው በተለይ የታወቁ ናቸው፡፡ እዚህ ላይ ‘ተባዕት ፍየሎች’ ጨቋኝ የነበሩትን የእግዚአብሔር ሕዝብ መሪዎች ይወክላሉ፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሠራዊት ጌታ ያህዌ ለመንጋው ለይሁዳ ቤትም ይጠነቀቃል

እዚህ ላይ ያህዌ ለሕዝቡ የሚያደርገው እንክብካቤ እረኛ ለበጎቹ እንደሚያደርገው እንክብካቤ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አት. “እረኛ ለበጎቹ እንክብካቤ እንደሚያደርግላቸው የሠራዊት ጌታ ያህዌ ለይሁዳ ቤት እንክብካቤ ያደርጋል”

የይሁዳ ቤት

‘ቤት’ የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ስመ-ምስል ስያሜ ነው፡፡ እዚህ ላይ የሚያመለክተው የይሁዳንና የቢንያምን ዝርያዎች የሚያካትተውን የይሁዳን ሕዝብ ነው፡፡ ትኩ. “ይሁዳ” ወይም “የይሁዳ ሕዝብ” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ጦርነት ፈረሶቹ ያደርጋቸዋል

ያህዌ የሕዝቡን ተለዋጭ ዘይቤ ተካላካይ ከሌላቸው በጎች ወደ ጦርነት ፈረሶች ይለውጣል፡፡ አት. “በውጊያ ላይ ብርቱ እንደሆኑ የጦርነት ፈረሶች ያደርጋቸዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ምስስሎሽ የሚሉትን ይመልከቱ)