am_tn/zec/10/01.md

2.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዘካርያስ ለእስራኤል ሕዝብ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ነገድጓዶችን ይፈጥራል

“ዝናብ እየጎረፈ የሚወጣባቸውን ደመናዎች ይፈጥራል”

በእርሻ ላይ ሰብል

“በእርሻ ላይ ሰብል እንዲበቅል ያደርጋል”

በቤት ውስጥ የተቀረጹ ጣዖቶች ሐሰት ይናገራሉ

“በቤት ውስጥ የተቀረጹ ጣዖቶች ሐሰተኛ መልእክት ይሰጣሉ” ዘካርያስ ጣዖቶች በእርግጥ ይናገራሉ የሚል ሃሳብ እየሰጠ አይደለም፡፡ ሰዎች ከጣዖቶች ሰማን እያሉ ስለሚናገሯቸው መልእክቶች እያመለከተ ነው፡፡ UDB ይህንን ግልጽ ያደርገዋል፡፡

ሟርተኞች የውሸት ራዕይ ያያሉ

“ሟርተኞች ሐሰት የሆነ ራዕይ ይመለከታሉ”

አታላይ ሕልሞችን ይናገራሉ

በግንዛቤ በተገኘው መረጃ መሠረት እነርሱ እነዚህ ሕልሞች ሐሰት እንደሆኑ ያውቃሉ፡፡ ይህንን በግልጽነት ማቅረብ ይቻላል፡፡ አት. “ሰዎችን ለማታለል ሲሉ ሟርተኞች ስለ ሕልማቸው ይዋሻሉ፡፡” (ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከንቱ መጽናናት

ለጊዜው የሚያባብሉ እንጂ ዘላቂ ዕርዳታ የማይሰጡ ቃላትን የሚያመለክት ነው፡፡

እንደ በጎች ይቅበዘበዛሉ

እውነቱን የሚናገሩ ነቢያት የሌላቸው ሕዝቦች ወዴት እንደሚሄዱ የሚነግራቸው እረኛ የሌላቸው በጎች እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አት. “ሐሰተኛ ነቢያትን የሚያዳምጡ ሕዝቦች በየት በኩል እንደሚሄዱ እንደማያውቁ በጎች ናቸው፡፡” (ምስስሎሽ የሚለውን ይመልከቱ)

እረኛ ስለሌላቸው ይሰቃያሉ

እውነቱን የሚናገሩ ነቢያት የሌላቸው ሕዝቦች ወዴት እንደሚሄዱ የሚነግራቸው እረኛ ስለሌላቸው የሚሰቃዩ በጎች እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አት. “ሐሰተኛ ነቢያትን የሚያዳምጡ ሕዝቦች የሚመራቸው እረኛ ስለሌላቸው እንደሚሰቃዩ በጎች ናቸው፡፡” (ምስስሎሽ የሚለውን ይመልከቱ)