am_tn/zec/09/16.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከቁ.14-16 ዘካርያስ እግዚአብሔር እስራኤልን ከጠላቶቿ እንዴት እንደሚያድናት ይገልጻል፡፡

እንደ ሕዝቡ መንጋ እግዚአብሔር ያድናቸዋል

የእስራኤል ሕዝብ የሚንከባከባቸውና የሚጠብቃቸው የእግዚአብሔር በጎች እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ (ምስስሎሽ የሚለውን ይመልከቱ)

የአክሊል ዕንቁዎች ናቸው

የእስራኤል ሕዝብ ምን ያህል የከበረ እንደሆነ በሚያመለክተው የንጉሡ አክሊል ላይ የተደረጉ ውድ ዕንቁዎች እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አት. “በአክሊል ላይ እንደተደረጉ ውብ የከበሩ ድንጋዮች ናቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ምን ያህል መልካምና ምን ያህል ውብ ይሆናሉ!

ይህ ቃለ-አጋኖ እንጂ ጥያቄ አይደለም፡፡ አት. “እጅግ መልካምና ውብ ይሆናሉ፡፡” (ቃለ-አጋኖ የሚለውን ይመልከቱ)

እህል ጎልማሶችን፣ ጣፋጭ ወይንም ደናግሉን ያሳምራል

ማንኛውም ሰው የተትረፈረፈ ምግብና መጠጥ እንደሚኖረው ለማመልከት ይህ ዓረፍተ ነገር የትይዩነት አወቃቀር ይጠቀማል፡፡ አንባቢዎቻችሁ ወንዶቹ ብቻ እንደሚበሉ፣ ሴቶቹ ብቻ እንደሚጠጡ የሚያስቡ ከሆነ አባባሉን መለወጥ ሊያስፈልጋችሁ ይችላል፡፡ አት. “ሁሉም ሰዎች፣ ወንዶችም ሴቶችም የተትረፈረፈ የሚበላና የሚጠጣ ይኖራቸዋል” (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

ጎልማሶቹ … ደናግሉ

ሁለቱ ቃላት ትይዩዎች ናቸው፣ በአንድነትም መላውን የእስራኤል ሕዘብ ይወክላሉ፡፡ (በከፊል የተወከለ አካል የሚለውን ይመልከቱ)

እህል … ጣፋጭ ወይን ጠጅ

ሁለቱ ቃላት ትይዩዎች ናቸው፣ በአንድነትም ሁሉንም የተለያዩ ምግቦችና መጠጦች ይወክላሉ፡፡ (ትይዩነት እና በከፊል የተወከለ አካል የሚሉትን ይመልከቱ)