am_tn/zec/09/14.md

3.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከቁ.14-16 ዘካርያስ እግዚአብሔር እስራኤልን ከጠላቶቿ እንዴት እንደሚያድናት ይገልጻል፡፡

ለእነርሱ ይገለጣል

‘ለእነርሱ’ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ሕዝብ ነው፡፡ አት. “በሰማይ ላይ በሕዝቡ ይታያል” ወይም “ወደ ሕዝቡ ይመጣል”

ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል!

እስራኤላውያን አንዳንድ ጊዜ የመብረቅ ብልጭታ እግዚአብሔር የሚወረውረው ቀስት እንደሆነ አድርገው ያስባሉ፡፡ (ምስስሎሽ የሚለውን ይመልከቱ)

መለከትን ንፉ

መለከቶች የአውራ በግ ቀንዶች ናቸው፡፡ ሰዎች በጦርነት ጊዜ ምልክቶችን ለመስጠት በሌሎችም አጋጣሚዎች ይነፏቸዋል፡፡ እዚህ ላይ መለከቱ የተነፋው ለጦርነት ምልክት እንዲሆን ነው፡፡

ከቴማንም ከዓውሎ ነፋስ ጋር ይጓዛል

ቴማን ከይሁዳ በስተደቡብ በኩል ያለ ስፍራ ነበር፡፡ እስራኤላውያን አንዳንድ ጊዜ ከደቡብ በሚነፍሰው ኃይለኛ ዓውሎ ነፋስ እንደሚጓዝ አድርገው ያስቡ ነበር፡፡ አት. “ከቴማን ከሚነፍሰው ዓውሎ ነፋስ ጋር ይጓዛል”

ይደመስሷቸዋል

“የይሁዳ ሕዝብ ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በድንጋይ ወንጭፍም ያሸንፋሉ

ለድንጋይ መወርወሪያ የሚጠቅሙ ወንጭፎች በዘካርያስ ዘመን የተለመዱ ነበሩ፡፡ እዚህ ላይ ‘የወንጭፍ ድንጋይ’ እስራኤልን ለማጥቃት የሚጠቀሙባቸውን ወታደሮችን ያመለክታል፡፡ አት. “በወንጭፍና በድንጋይ የሚያጠቋቸውን ጠላቶች ድል ያደርጋል” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያ በኋላም ይጠጣሉ፣ ወይን ጠጅ ጠጥቶ እንደሰከረ ሰውም ይጮኸሉ

የይሁዳ ሕዝብ እንደ ጯኺ ሰካራሞች በጠላቶቻቸው ላይ ስላገኙት ድል ይጮኸሉ፣ ድላቸውንም ያከብራሉ፡፡ አት. “ከዚያ በኋላ ይጮኸሉ፣ እንደ ሰከሩ ሰዎችም ድላቸውን በጩኸት ያከብራሉ” (ምስስሎሽ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ወጭት በወይን ጠጅ ይሞላሉ

ይህ ምናልባት ካህናት የእንሰሶችን ደም ወደ መሠዊያ ለመውሰድ የሚጠቀሙበትን ወጭት ሳያመለክት አይቀርም፡፡ አት. “ካህናት ደሙን ወደ መሠዊያ እንደሚወስዱባቸው ወጭቶች በወይን ጠጅ የተሞሉ ይሆናሉ፡፡” (ምስስሎሽ፣ ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

የመሠዊያውን ማዕዝኖች

መሠዊያዎች ወደ ውጭ ወጣ ወጣ ያሉ በእንሰሳ ደም የረሰረሱ ማዕዝኖች አሏቸው፡፡ አት. “የመሠዊያው ማዕዝኖች በደም የተነከሩ እንደሆኑ ሁሉ እነርሱም እንደዚሁ የረሰረሱ ይሆናሉ” (ምስስሎሽ፣ ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)