am_tn/zec/09/11.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከቁ.9-13 ተናጋሪው ያህዌ ይመስላል፡፡

አንቺ ጽዮን

እዚህ ላይ ‘አንቺ’ የሚለው ነጠላ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተውም ‘ጽዮን’ እየተባለችም የምትጠራውን የኢየሩሳሌምን ከተማ ነው፡፡

ውሃ ከሌለበት ጉድጓድ

ይህ ደረቅ ጉድጓድ የባቢሎን ስደትን ይወክላል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ምሽጎቻችሁ ተመለሱ

ኢየሩሳሌም ደህንነት ያለባት ስፍራ እንደሆነች እየተነገረ ነው፡፡ አት. “ደህንነታችሁ ወደሚጠበቅበት ወደ አገራችሁ ተመለሱ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የተስፋ እስረኞች

አገላለጹ በምርኮ ላይ ሳሉ እግዚአብሔር ገና ያድነናል ብለው ሲያምኑ የነበሩትን እስራኤላውያንን ያመለክታል፡፡ ትኩ. “በያህዌ ላይ ገና ያምኑ የነበሩ እስረኞች”

ሁለት እጥፍ አድርጌ እመልስላችኋለሁ

“ከእናንተ የተወሰደው እጥፍ ሆኖ ይመለስላችኋል”

ይሁዳን እንደ ቀስቴ እገትረዋለሁ

የይሁዳ ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ጦርነት እንደወሰደው ቀስት እንደሆኑ ተደርገው ተጠቅሰዋል፡፡ እዚህ ላይ ‘ይሁዳ’ የዚያ አገር ሕዝቦችን ያመለክታል፡፡ አት. “የይሁዳ ሕዝቦች እንደ ቀስቴ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ስመ-ምስል ስያሜ የሚሉትን ይመልከቱ)

በኤፍሬምም ኮረጆዎቼን እሞላለሁ

ያህዌ የሰሜኑን መንግሥት የእስራኤልን ሕዝብ በጠላቶቹ ላይ የሚወረውራቸው ቀስቶች እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ ኮርጆ አንድ ወታደር ቀስቶቹን የሚይዝበት ከረጢት ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጽዮን ሆይ፣ ልጆችሽን አስነሣለሁ፣ ግሪክ ሆይ፣ በአንቺ ላይ

እግዚአብሔር በአንድ ጊዜ ለሁለት የተለያዩ አገር ሕዝቦች እየተናገረ ነው፡፡ (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)