am_tn/zec/09/09.md

3.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከቁ.9-13 ባሉት ተናጋሪው ያህዌ ይመስላል፡፡

የጽዮን ልጅ ሆይ፣ በታላቅ ሐሴት ድምፅሽን አሰሚ፣ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ በደስታ እልል በዪ

የእነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ነው፣ ሁለቱም ደስ እንዲላቸው የተሰጠውን ትዕዛዝ ያጠናክራሉ፡፡ ያህዌ የኢየሩሳሌም ሕዝቦች እዚያ እንደነበሩ አድርጎ እየተናገረ ነው፣ እነርሱ ግን እዚያ አልነበሩም፡፡ (ትይዩነት እና የሌለን እንዳለ አድርጎ መናገር የሚሉትን ይመልከቱ)

የጽዮን ሴት ልጅ፣ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ

‘ጽዮን’ እና ‘ኢየሩሳሌም’ አንድ ናቸው፡፡ ነቢዩ ስለ ከተማይቱ ሴት ልጅ እንደሆነች አድርጎ እየተናገረ ነው፡፡ በዘካርያስ 2፡10 ላይ የጽዮን ሴት ልጅ የሚለውን እንዴት እንደተረጎማችሁት ዞር ብላችሁ ተመልከቱ፡፡

እነሆ

ይህ አንባቢው ለሚቀጥለው አስደናቂ ገለጻ የተለየ ትኩረት እንዲሰጥ ያሳስበዋል፡፡ አት. “ልብ በል” ወይም “እዚህ ላይ አስደናቂ እውነታ አለ”

ንጉሥሽ ወደ አንቺ በጽድቅ ይመጣል፣ያድንሽማል

“ንጉሥሽ ጻድቅ ነው፣ የሚመጣውም ሊያድንሽ ነው፡፡”

በአህያ ላይ በአህያይቱም ውርንጫ ላይ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ አንድ ዓይነት ትርጉም ያላቸው ናቸው፣ የሚናገሩትም ስለ አንድ እንሰሳ ነው፡፡ ሁለተኛው ሐረግ ግልገል አህያ እንደሆነ መግለጫ ይሰጣል፡፡ አት. “በግልገል አህያ ላይ” (ጥምር አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ሠረገላውንም ከኤፍሬም እቆርጣለሁ

እዚህ ላይ ‘እቆርጣለሁ’ የሚለው እደመስሳለሁ የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ አባባል ነው፡፡ አት. “በእስራኤል ያሉትን ለጦርነት የሚያገለግሉትን ሠረገሎች እደመስሳለሁ”

ፈረሶችንም ከኢየሩሳሌም

ስለ ‘ሠረገላ’ እና ስለ ‘ቀስት’ መጠቀሱ ፈረሶቹ ለጦርነት የሚያገለግሉ እንደነበሩ ያመለክታል፡፡ ይህንን ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አት. “በኢየሩሳሌም ያሉት የውጊያ ፈረሶች” (ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ቀስቱ ከውጊያ ይቆረጣል

እዚህ ላይ ቀስት በጦርነት ጥቅም ላይ የሚውሉትን መሣሪያዎች ይወክላል፡፡ አት. “የጦር መሣሪያዎች ሁሉ ይደመሰሳሉ” (በከፊል የተወከለ አካል የሚለውን ይመልከቱ)

ሰላምን ለሕዝቦች ይናገራል

እዚህ ላይ ሰላምን የማወጅ ተግባር ሰላም የማድረግን ተግባር ይወክላል፡፡ አት. “ንጉሣችሁ ለሕዝቦች ሰላምን ያመጣላቸዋል” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፣ ከወንዙ እስከ ምድር ዳርቻ ይሆናል

‘ከባሕር እስከ ባሕር’ እና ‘ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ’ የሚሉት ሐረጎች ትርጉማቸው አንድ እንደመሆኑ በአንድ ላይ ሊጣመሩ ይችላሉ፡፡ አት. “መንግሥቱ በመላው ምድር ላይ ይሆናል” (ጥምር አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ወንዙ

ይህ ምናልባት የኤፍራጥስን ወንዝ ሳያመለክት አይቀርም፡፡