am_tn/zec/09/05.md

1.5 KiB

አስቀሎና፣ ጋዛ፣ አቃሮንም … ተስፋዋ

እነዚህ ከተሞች እያንዳንዳቸው በውስጣቸው የሚኖሩ ሕዝቦችን ያመለክታሉ፡፡ አት. “የአስቀሎና ሕዝቦች … የጋዛ ሕዝቦች … የአቃሮን ሕዝቦች ተስፋዎች” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

አይታ

ጢሮስ ስትወድም ታያለች

እንግዶች ቤታቸውን በአሽዶድ ያደርጋሉ

“እንግዶች አሽዶድን ወስደው በዚያ ይኖራሉ”

የፍልስጥኤማውያንንም ትምክህት እቆርጣለሁ

እዚህ ላይ ‘እቆርጣለሁ’ የሚለው ትምክህታቸውን አስቆማለሁ የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ አባባል ነው፡፡ አት. “ፍልስጥኤማውያን ከእንግዲህ በራሳቸው እንዳይመኩ አደርጋቸዋለሁ፡፡” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ደሙን ከአፋቸው ነውራቸውንም ከጥርሳቸው መካከል አወጣለሁ

እዚህ ላይ ‘ደም’ ደም በውስጡ ላለበት ሥጋ፣ ‘ነውር’ ደግሞ ለጣዖት ለቀረበ ሥጋ ስመ-ምስል ስያሜዎች ናቸው፡፡ አት. “በውስጡ ደም ያለበትን ሥጋ ከእንግዲህ እንዲበሉ አልፈቅድላቸውም፣ ለጣዖት የሚያቀርቡትንም ምግብ እንዳይበሉ እከለክላቸዋለሁ” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)