am_tn/zec/09/03.md

1.7 KiB

ለራሷ ምሽግ ሠርታለች

እዚህ ላይ የጢሮስ ከተማ በሴት ተመስላለች፡፡ አት. “ጠንካራ ምሽግ ሠርታለች” ወይም “ከፍ ያለ ቅጥር ሠርታለች” (ሰውኛ የሚለውን ይመልከቱ)

ብርን እንደ አፈር የነጠረንም ወርቅ እንደ መንገድ ላይ ጭቃ ቆልላለች

ጢሮስ ምን ያህል ባለጠጋ እንደነበረች አጽንዖት ለመስጠት ያህዌ የግነት አነጋገር ይጠቀማል፡፡ አት. “በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ብርንና ወርቅን አከማችታለች” (ግነት እና ጥቅል አባባል የሚባሉትን ይመልከቱ)

እነሆ፣ ጌታ ይወስድባታል

እዚህ ላይ ‘እነሆ’ የሚለው ቃል ተአንባቢው ለሚቀጥለው አስፈላጊ ገለጻ ትኩረት እንዲሰጥ ያሳስበዋል፡፡ አት. “አስተውል! ጌታ የጢሮስን ሀብት ይወስድባታል፡፡”

በባሕር ላይ ያላትን ኃይል ይደመስሳል

‘በባሕር ላይ ያላት ኃይል’ የሚያመለክተው ለንግድና ለወረራ የሚውሉትን መርከቦች ነው፡፡ አት. “ሰዎች በባሕር ላይ ውጊያ የሚያካሂዱባቸውን የጢሮስን መርከቦች ይደመስሳል” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

በእሳት ፈጽማ ትጠፋለች

ይህ በተናጋሪ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት. “ጠላቶች ከተማይቱን እስክትወድም በእሳት ያቃጥሏታል” (ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚለውን ይመልከቱ)