am_tn/zec/09/01.md

2.0 KiB

… በሚመለከት ይህ የያህዌ ቃል አዋጅ ነው

“ይህ ስለ … የያህዌ መልእክት ነው”

የሴድራክና የደማስቆ ምድር

እዚህ ላይ ‘ሴድራክ’ እና ‘ደማስቆ’ በእነዚያ ስፍራዎች የሚኖሩትን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡ አት. “የሴድራክ ምድርና የደማስቆ ከተማ ሕዝቦች” (ስመ-ምስል ስያሜ እና ስሞችን እንዴት መተርጎም እንደሚገባ የሚሉትን ይመልከቱ)

ሴድራክ

የሴድራክ አድራሻ አሁን የት እንደሆነ አይታወቅም፡፡

ማረፊያ ቦታው

“የሴድራክ ሕዝብ ማረፊያ ቦታ”

የሰዎች ሁሉና የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ዓይኖች ወደ እግዚአብሔር አቅንቷል

እዚህ ላይ ‘ዓይኖች’ የሚመለከቱትን ነገር ያመለክታል፡፡ አት. “የሰው ልጆች ሁሉና የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ወደ ያህዌ ይመለከታሉ፡፡” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

ሐማት

ይህ በዚያ ምድር የሚኖሩትን ሕዝቦች ያመለክታል፡፡ አት. “የሐማት ምድር ሰዎች” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

ጢሮስና ሲዶና

ይህ በዚያ ምድር የሚኖሩትን ሕዝቦች ያመለክታል፡፡ አት. “የጢሮስና የሲዶና ምድር ሰዎች” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

በጣም ጥበበኞች ስለሆኑ

ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፡ - 1) ለዕርዳታ ወደ ያህዌ በመመልከታቸው ሕዝቡ ጠቢባን ናቸው ወይም 2) ዘካርያስ የሐማት ሰዎች በእርግጥ ጠቢባን ነበሩ ማለቱ ሳይሆን ሽሙጥ አነጋገር እየተጠቀመ ነበር፡፡ ትኩ. “ምንም እንኳን በጣም ጠቢባን ነን እያሉ የሚያስቡ ቢሆኑም” (ሽሙጥ የሚለውን ይመልከቱ)