am_tn/zec/07/08.md

1.7 KiB

የያህዌ ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ … እንዲህም አለው ‘ያህዌ …’

ይህ ፈሊጣዊ አባባል አንድ የተለየ መልእክትን ለማሰተዋወቅ ጥቅም ላይ የዋለ ነው፡፡ አት. “ያህዌ ለዘካርያስ መልእክት ሰጠው፣ እንዲህም አለው ‘ያህዌ’” ወይም “ያህዌ ይህንን መልእክት ለዘካርያስ ነገረው፡ - ‘ያህዌ’” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

በእውነተኛ ፍትሕ ዳኙ፣ ታማኝነትንና ምሕረትን አድርጉ

የነገር ስም የሆኑት ‘ፍትሕ’፣ ‘ታማኝነት’ እና ‘ምሕረት’ በቅጽል መልክ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አት. “በምትዳኙበት ጊዜ፣ ፍትሐዊ ሁኑ፣ ለኪዳኑ ታማኝ፣ መሐሪም ሁኑ” (የነገር ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱ ሰው ይህንን ያድርግ

‘ይህንን’ የሚለው ቃል እያንዳንዱ ሰው እንዴት መዳኘት እንዳለበት የሚያመለክት ነው፡፡

መበለት

ባሏ የሞተባት ሴት

ድኀ-አደግ (ወላጁን-ያጣ)

ወላጆቹ የሞቱበት ልጅ

መጻተኛ

ከራሱ አገር ወደ ሌላ አገር የሄደ ሰው

ከእናንተ ማንኛችሁም በሌላው ላይ በልባችሁ ክፉ ነገር አታስቡ

እዚህ ላይ ‘ልብ’ የሚለው የአንድን ሰው ሃሳብ ይወክላል፡፡ አት. “ክፋትን ለማድረግ ዕቅድ ማቀድ የለባችሁም” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)