am_tn/zec/07/04.md

4.0 KiB
Raw Permalink Blame History

የሠራዊት ጌታ የያህዌ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ … ተናገር

ይህ ፈሊጣዊ አባባል አንድ የተለየ መልእክትን ለማሰተዋወቅ ጥቅም ላይ የዋለ ነው፡፡ አት. “የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ የሚል መልእክት ሰጠኝ፡ ‘…ተናገር’” ወይም “የሠራዊት ጌታ ያህዌ ይህንን መልእክት ነገረኝ፡ ‘…ተናገር’” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

በአምስተኛው ወርና በሰባተኛው ወር

5ተኛውና 7ተኛው ወሮች ሲሆኑ’ (መደበኛ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

በአምስተኛው

‘ወር’ የሚለው ቃል በመተርጎም ወቅት ሊጨመር ይችላል፡፡ አት. “በአምስተኛው ወር” (ግድፈት የሚለውን ይመልከቱ)

በሰባተኛው ወር

በግምታዊው እውቀት መሠረት የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ላይ ገዢ አድርጎ ከሾመው ከጎዶልያስ መገደል በኋላ በኢየሩሳሌም ቀርተው የነበሩት አይሁድ ወደ ግብፅ የሸሹት በዚህ ወር ስለነበረ አይሁድ ያለቅሱ ነበር፡፡ ሰባተኛው ወር በአውሮፓውያን (ጊሪጎሪያን) አቆጣጠር በመስከረም ወር መጨረሻና በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ይውላል፡፡ (ግምታዊ እውቀት፣ ውስጠ-ታዋቂ መረጃ እና የዕብራውያን ወሮች የሚሉትን ይመልከቱ)

ለእነዚህ ሰባ ዓመታት

በግምታዊው እውቀት መሠረት የእስራኤል ሕዝቦች በባቢሎን ለሰባ ዓመታት ባሪያዎች ሆነው ነበር፡፡ (ግምታዊ እውቀት፣ ውስጠ-ታዋቂ መረጃ እና ቁጥሮች የሚሉትን ይመልከቱ)

የጾማችሁት በእርግጥ ለእኔ ነበርን?

ጥያቄው የተጠየቀው ሕዝቡ የመጾማቸው እውነተኛ ምክንያት ምን እንደነበረ እንዲያስቡ ለማድረግ ነው፡፡ በገለጻ መልክ ሊተረጎም ይችላል፡ -አት. “በእርግጥ ትጾሙ የነበረው ለእኔ አልነበረም” (መልስ የማያጠብቅ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ትበሉና ትጠጡ የነበረው

ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፡ 1) ሃይማኖታዊ በዓላትን ሲያከብሩ ፈንጠዝያ ያደርጉና ይጠጡ የነበሩት፣ ወይም 2) በማይጾሙበት ጊዜ ሁሉ ሲበሉና ሲጠጡ የነበሩት

ትበሉና ትጠጡ የነበረው ለራሳችሁ አልነበረምን?

ጥያቄው የተጠየቀው ሕዝቡ በሚበሉበትና በሚጠጡበት ጊዜ ያህዌ ያከብሩ እንደነበረ ወይም እንዳልነበረ እንዲያስቡ ለማድረግ ነው፡፡ አት. “ትበሉና ትጠጡ የነበራችሁት ለራሳችሁ ነበር” (መልስ የማያጠብቅ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የተናገረው ቃል ይህ አልነበረምን … ለምዕራብ

ያህዌ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት ሕዝቡን ለመዝለፍ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በገለጻ መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት. “እነዚህ ተመሳሳይ ቃላት ናቸው … ለምዕራብ” (መልስ የማያጠብቅ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በቀደሙት ነቢያት አንደበት

እዚህ ላይ ‘አንደበት’ የሚለው በአንደበት ለተነገረው ቃል ስም-ምስል ስያሜ ነው፡፡ አት. “በቀደሙት ነቢያት ቃል” ወይም “በቀደሙት ነቢያት በኩል” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

አሁንም በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ናችሁ

“አሁንም በኢየሩሳሌም እየኖራችሁ ነው”

ኮረብቶች ግርጌ

ከተራራው ወይም ከሰንሰለታማ ተራሮች በስተግርጌ ያሉ ኮረብቶች