am_tn/zec/07/01.md

2.2 KiB

በአራተኛው ቀን

‘አራተኛው ቀን ሲሆን’ (መደበኛ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ካሴሉ

‘ካሴሉ’ በዕብራውያን ዘመን አቆጣጠር ዘጠነኛው ወር ነው፡፡ የካሴሉ ወር በአውሮፓውያን (በጊሪጎርያን) ዘመን አቆጣጠር ወደ ኅዳር ወር መጨረሻ አካባቢ ነው፡፡ (የዕብራውያን ወሮች እና ስሞችን እንዴት መተርጎም እንደሚገባ የሚሉትን ይመልከቱ)

የያህዌ ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ

ይህ ፈሊጣዊ አባባል አንድ የተለየ መልእክትን ለማሰተዋወቅ ጥቅም ላይ የዋለ ነው፡፡ አት. “ያህዌ ለዘካርያስ መልእክት ሰጠው’” ወይም “ያህዌ ይህንን መልእክት ለዘካርያስ ነገረው” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ሳራሳርና ሬጌሜሌክ

እዚህ ላይ ‘መለመን’ ማለት መማፀን ወይም አጣዳፊ ጥያቄ ማቅረብ ማለት ነው፡፡

በያህዌ ፊት

እዚህ ላይ ‘ፊት’ የሚለው ለያህዌ ሕላዌ ስመ-ምስል ስያሜ ነው፡፡ አት. “ያህዌ በተገኘበት” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

በአምስተኛው ወር ማዘን … ይገባኛል

“5ተኛው ወር በሚሆንበት ጊዜ ማዘን ይገባኛል?” በግምታዊው እውቀት መሠረት በኢየሩሳሌም የነበረው ቤተ መቅደሱ በባቢሎናውያን የፈረሰው በዚህ ወር ስለነበረ የአይሁድ ሕዝቦች በዕብራውያን ዘመን አቆጣጠር በአምስተኛው ወር በከፊል ይጾሙ ነበር፡፡ አምስተኛው ወር በአውሮፓውያን (ጊሪጎሪያን) አቆጣጠር በሐምሌ ወር መጨረሻና በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ይውላል፡፡ (መደበኛ ቁጥሮች፣ ግምታዊ እውቀት፣ ውስጠ-ታዋቂ መረጃ እና የዕብራውያን ወሮች የሚሉትን ይመልከቱ)

በጾም አማካይነት

‘በመጾም’