am_tn/zec/05/08.md

1.9 KiB

ይህች ርኩሰት ናት

ሴትዮዋ ርኩሰትን ትወክላለች፡፡ አት. “ይህች ሴት ርኩሰትን ትወክላለች” (ተምሳሌታዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

መልሶ አስገባት … የእርሳሱንም ክዳን …ገፍቶ

“መልሶ አስገባት … የእርሳሱንም ክዳን ገፍቶ” ‘መልሶ አስገባት’ ወይም ‘ወረወራት’ የሚለው ቃል መልአኩ እነዚህን ነገሮች በእንዴት ያለ ኃይል እንዳከናወነ ያመለክታል፡፡ ሴቲቱንም ሆነ ክዳኑን ቃል በቃል አልወረወራቸውም፡፡

ዓይኖችህን አንሣ

‘ዓይኖች’ የሚለው ቃል የሚወከለው የሚመለከተውን ሰው ነው፡፡ አት. “ወደ ላይ ተመልከት” (በክፋይ የተወከለ አካል የሚለውን ይመልከቱ)

በክንፎቻቸውም ንፋስ ነበረ

ይህ ፈሊጣዊ አባባል ይበሩ ነበር የሚል ትርጉም አለው፡፡ አት. “ይበሩ ነበር” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ

ሽመላ ከሁለት እስከ አራት ሜትር ርዝመት የሚሆን ክንፍ ያለው ትልቅ የወፍ ዘር ነው፡፡ ዘካርያስ የሴትዮዋን ክንፍ ስፋት መጠን ከሽመላ ክንፍ ጋር ያነጻጽረዋል፡፡

ቅርጫቱንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት

‘ምድር’ እና ‘ሰማይ’ የሚሉት ቃላት ሰማይን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋሉ የ… ዓይነት ናቸው፡፡ ሁለቱ ሴቶች ከቅርጫቱ ጋር መብረራቸው ውስጠ-ታዋቂ ነው፡፡ አት. “ቅርጫቱን ወደ ሰማይ አነሱትና በረሩ” (…ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)