am_tn/zec/05/05.md

1.7 KiB

ዓይኖችህን አንሣ

‘ዓይኖች’ የሚለው ቃል የሚወከለው የሚመለከተውን ሰው ነው፡፡ አት. “ወደ ላይ ተመልከት” (በክፋይ የተወከለ አካል የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ሊመጣ ያለውን ኢፍ የያዘ ቅርጫት ነው

‘ኢፍ’ ደረቅ ነገሮች የሚለኩበት የልኬት መስፈሪያ ሲሆን መጠኑም 2.2 ሊትር ነው፡፡ እዚህ ላይ ቃሉ አንድ ኢፍ ደረቅ ነገሮች ለሚይዘው መስፈሪያ ስመ-ምስል ስያሜ ነው፡፡ አት. “ይህ ሊመጣ ያለው የመለኪያው ቅርጫት ነው” ወይም “ይህ ሊመጣ ያለው ትልቅ መስፈሪያ ነው” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ የፍሳሽ መጠን እና ስመ-ምስል ስያሜ የሚሉትን ይመልከቱ)

በምድሪቱ ሁሉ ላይ ያለው የሕዝቡ በደል

ቅርጫቱ የሕዝቡን በደል በተምሳሌትነት ይወክላል ነገር ግን ቃል በቃል በደላቸው አይደለም፡፡ አት. “ይህ ቅርጫት በመላው ምድሪቱ ያሉትን ሰዎች በደል ይወክላል፡፡” (ተምሳሌታዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ከእርሳስ የተሠራው ክዳን ተነሣ

ይህ በተናጋሪ መልኩ ሊቀርበ ይችላል፡፡ አት. “አንድ ሰው ከቅርጫቱ ላይ የእርሳሱን ክዳን አነሣ” (ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከበታቹም በውስጡ የተቀመጠች ሴት ነበረች

“ከእርሳሱ ክዳን በታች በቅርጫቱ ውስጥ የተቀመጠች ሴት ነበረች”