am_tn/zec/05/03.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከዘካርያስ ጋር የሚነጋገረው መልአክ ራዕዩን መግለጹን ይቀጥላል፡፡

ይህ … እርግማን ነው

‘ይህ’ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የመጽሐፉን ጥቅልል ነው፡፡ የመጽሐፉ ጥቅልል በጥቅልሉ ውስጥ ለተጻፈው ስመ-ምስል ስያሜ ነው፡፡ አት. “በዚህ መጽሐፍ ጥቅልል ውስጥ ያለው እርግማን ነው፡፡” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ በምድር ሁሉ የሚወጣ

‘በምድር ሁሉ’ የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው በምድሩ ያለውን ማንኛውንም ስፍራ ነው፡፡ ርግማኑ በምድሪቱ ውስጥ በሚኖር በማንኛውም ሰው ላይ እንደሚደርስ ይጠቁማል፡፡ አት. “በመላ ምድሪቱ ባለ ማንኛውም ሰው ላይ ማለት ነው” (ፈሊጣዊ አባባል፣ ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

የሚሰርቅ ሁሉ ይጠፋል … በሐሰት የሚምል ሁሉ ይጠፋል

እነዚህን ሕዝቦች ከምድሪቱ የሚያስወግደው ያህዌ አንድ ሰው ከዛፍ ላይ ቅርንጫፍ እንደሚቆርጥ ሲቆርጣቸው እንደነበረ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ይህ በተናጋሪ መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡ አት. “ያህዌ ማንኛውንም ሌባ ያስወግዳል … ያህዌ በሐሰት መሐላ የሚምለውን ሁሉ ያስወግዳል” ወይም “ያህዌ ማንኛውንም ሌባ ከምድሪቱ ያስወግዳል … ያህዌ ከምድሪቱ በሐሰት የሚምለውን ማንኛውንም ሰው ያስወግዳል፡፡” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚሉትን ይመልከቱ)

በአንድ በኩል የሚለውን … በሌላ በኩል የሚለውን

“የመጽሐፉ ጥቅልል በአንድ በኩል የሚለው … የመጽሐፉ ጥቅልል በሌላ በኩል የሚለው”

አመጣዋለሁ

“እልከዋለሁ”

ያህዌ … እንዲህ ይላል

እያወጀ ያለውን ነገር እርግጠኛነት ለመግለጽ ያህዌ ስለ ራሱ ስሙን በመጥቀስ ይናገራል፡፡ በዘካርያስ 1፡4 ላይ ተመሳሳይ የሆነውን ሐረግ እንዴት እንደተረጎማችሁት ዞር ብላችሁ ተመልከቱ፡፡ አት. “የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንደዚህ ብሎ ተናግሯል” ወይም “እኔ የሠራዊት ጌታ ያህዌ የምናገረው ይህንን ነው” (‘መጀመሪያ፣ ሁለተኛ፣ ሶስተኛ ሰው’ የሚለውን ይመልከቱ)

እንጨቱንና ድንጋዩን ያጠፋል

የሌባውንና በሐሰት የሚምለውን ቤቶች የሚያጠፋው ርግማን ሰዎቹ የሚኖሩባቸው ቤቶች የተሠሩባቸውን የሕንፃ ቁሳቁሶች እንደሚያቃጥል ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አት. “እንጨቱንና ድንጋዩን ያጠፋል” ወይም “ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ እና በክፋይ የተወከለ አካል የሚለውን ይመልከቱ)