am_tn/zec/04/08.md

3.6 KiB

አያያዥ መግለጫ

ከዘካርያስ ጋር የሚነጋገረው መልአክ ራዕዩን መግለጹን ይቀጥላል፡፡

የያህዌ ቃል ወደ እኔ መጣ እንዲህ ሲል፡ - “የዘሩባቤል አጆች …”

ፈሊጣዊው አባባል ጥቅም ላየ የዋለው ከእግዚአብሔር የመጣን የተለየ መልእክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ አት. “እግዚአብሔር መልእክትን ሰጠኝ፣ እንዲህም አለኝ፡ - ‘የዘሩባቤል እጆች …’” ወይም “ያህዌ ይህንን መልእክት ነገረኝ፡ - ‘የዘሩባቤል እጆች …’” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

የዘሩባቤል እጆች … መሠረት ጣሉ … የሚፈጽሙትም የእርሱ እጆች ናቸው

እዚህ ላይ ‘እጆች’ የሚለው ቃል የሚወክለው ዘሩባቤልን ነው፡፡ አት. “ዘሩባቤል መሠረቱን ጥሏል … የሚፈጽመውም እርሱ ነው፡፡” (በክፋይ የተወከለ አካል የሚለውን ይመልከቱ)

የዚህን ቤት መሠረት

እዚህ ላይ ‘ቤት’ የሚለው ቃል የሚወክለው ቤተ መቅደሱን ነው፡፡ አት. “የዚህ ቤተ መቅደስ መሠረት” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? ይህ ሕዝብ ይደሰታል

ዘካርያስ ይህንን መልስ የማይጠብቀውን ጥያቄ የተጠቀመበት በተለይ ‘የጥቂቱን ነገር ቀን’ ስለናቁት ለመናገር ነው፡፡ አባባሉ በገለጻ መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት. “የጥቂቱን ነገር ቀን የናቁ ይደሰታሉ” (መልስ የማይጠብቅ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የጥቂት ነገሮች ቀን

‘የጥቂት ነገሮች ጊዜ’ ይህ ሐረግ የሚያመለክተው ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን ሲገነቡ የነበሩበትንና ጥቂት እርምጃ እያሳዩ የመሰሉበትን ጊዜ ነው፡፡ አት. “የሥራው እርምጃ ዘገምተኛ የነበረበት ጊዜ” (ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ቱንቢው

ይህ የሚያመለክተው የሕንፃው ግድግዳዎች ትክክል መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሕንፃውን የሚገነቡ የሚጠቀሙበት ከገመድ ጫፍ ከባድ ነገር የታሠረበት መሣሪያ ነው፡፡

እነዚህ ሰባት መቅረዞች … ሁለት የወይራ ዛፎች

እነዚህ የሚያመለክቱት ዘካርያስ በዘካ.4፡2-3 ላይ የተመለከታቸውን ሰባት መቅረዞችና ሁለት የወይራ ዛፎችን ነው፡፡

እነዚህ ሰባቱ መቅረዞች በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የያህዌ ዓይኖች ናቸው

እነዚህ ሰባት መቅረዞች በተምሳሌትነት የያህዌን ዓይኖች ይወክላሉ፣ ነገር ግን ቃል በቃል የያህዌ ዓይኖች አይደሉም፡፡ መልአኩ የይህዌ ዓይኖች በመላው ምድር እንደሚዘዋወሩ አድርጎ የያህዌ ዓይኖች በምድር የሚደረገውን ሁሉ እንደሚመለከቱ ይና ገራል፡፡ አት. “እነዚህ ሰባት መቅረዞች በመላው ምድር የሚደረገውን ማንኛውንም ነገር የሚመለከቱትን የያህዌን ዓይኖች ይወክላሉ፡፡” (ተምሳሌታዊ ቋንቋ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)