am_tn/zec/03/06.md

1.8 KiB

አበክሮ ኢያሱን አዘዘው

ጠበቅ ባለ ሁኔታ ኢያሱን አዘዘው፡፡

በመንገዴ ብትሄድ ትዕዛዜንም ብትጠብቅ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ አንድ ናቸው፡፡ ያህዌ ስለ መታዘዝ የሚናገረው ሰውዬው በያህዌ መንገድ ላይ እንደሚራመድ አድርጎ ነው፡፡ አት. “የምትታዘዘኝ ከሆነና ትዕዛዜን የምትጠብቅ ከሆነ” (ትይዩነት እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ቤቴን ታስተዳድራለህ በአደባባዮቼም ላይ ኃላፊ ትሆናለህ

እዚህ ላይ ‘ቤቴ’ የሚለው ቃል ለቤተ መቅደሱ ምስለ-ምስል ስያሜ ሲሆን ‘አደባባዮቼ’ የሚለው ቃል ደግሞ የሚያመለክተው በቤተ መቅደሱ ዙሪያ የነበረውን ግቢ ነው፡፡ ቃላቱ በአንድነት ኢያሱ በአጠቃላይ በቤተ መቅደሱ ይዞታ ላይ ሥልጣነ ይኖረዋል የሚል ትርጉም አላቸው፡፡ አት. “በመቅደሴና በቅጥር ገቢው ላይ ሥልጣን ይኖርሃል” (ምስለ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

በፊቴ በሚቆሙት መካከል ትገባና ትወጣ ዘንድ

‘…መካከል ትገባና ትወጣ ዘንድ’ የሚለው ሐረግ ኢያሱ ወደ ያህዌ ዘንድ የመግባት መብት ያለው ቡድን አካል እንደሚሆንና ከእነርሱም እኩል መብት እንደሚኖረው የሚገልጽ ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ አባባል ነው፡፡ አት. “እነዚህ በፊቴ ያሉት እንደሚመጡ ሁሉ በፊቴ ትመጣ ዘንድ” (ፈሊጣዊ አባባል፣ ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)