am_tn/zec/03/04.md

1.5 KiB

ከፊቱ ቆመው የነበሩትን

በፊቱ በሚለው በውስጠ-ታዋቂ ‘ከእርሱ’ (ፊት) የሚለው ቃል የሚያመለክተው መልአኩን ነው፡፡ ቃሉ የሚያመለክተው በዚያ የነበሩትን ሌሎች መላእክትን ነው፡፡

እነሆ (አስተውል)

“ልነግርህ ያለሁት እውነተኛና አስፈላጊም ስለሆነ ልብ አድርገው”

ኃጢአትህን ከአንተ አስወግጃለሁ

የኢያሱ ልብሶች የኃጢአተኛነት ተምሳሌት ስለነበሩ፣ ልብሱን በማስወገድ መልአኩ የኢያሱን ኃጢአተኛነት እያስወገደ ነበር፡፡ ኃጢአትን ማስወገድ የሚለው አገላለጽ ፈሊጣዊ አባባል ሲሆን ትርጉሙም የኢያሱን በደል ከእርሱ አርቆለታል ማለት ነው፡፡ አት. “ኃጢአትህን ከአንተ አርቄያለሁ” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ

እዚህ ላይ ‘ጥሩ ልብስ’ በተምሳሌትነት የሚወክለው ጽድቅን ነው፡፡ (ተምሳሌታዊ ቋንቋ የሚለውን ይመልከቱ)

አድርጉለት

እዚህ ላይ በውስጠ-ታዋቂ ‘እነርሱ’ (ያድርጉለት) የሚለው የሚያመለክተው በዚያ የነበሩትን ሌሎች መላእክት ነው፡፡

ጥምጥም

በራስ ላይ የሚጠመጠም ረጅም የጨርቅ ቁራጭ