am_tn/zec/03/01.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለዘካርያስ ስለ ካህኑ ስለ ኢያሱ ራዕይ ያሳየዋል፡፡

ስለ ኃጢአት ሊከሰው በቀኙ በኩል ቆሞ ነበር

“ኢያሱን ስለ ኃጢአት ሊከሰው ዝግጁ ሆኖ ሰይጣን ከኢያሱ በስተቀኝ ቆሞ ነበር፡፡”

ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትግታግ አይደለምን?

የያህዌ መልአክ ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የጠየቀው ለሚጠበቀው አዎንታዊ ምላሽ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ አባባል በገለጻ መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡ አት. “ኢያሱ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ ነው፡፡” (ምላሽ የማይጠብቅ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእሳት የተነጠቀ ትግታግ

ትንታግ እየተቃጠለ ያለ ጉርማጅ እንጨት ነው፡፡ የያህዌ መልአክ ኢያሱ ከባቢሎን ምርኮ ተርፎ መምጣቱን እንጨቱ ሙሉ በሙሉ ከመቃጠሉ በፊት አንድ ሰው ከእሳት ውስጥ መዞ እንዳወጣው እየተናገረ ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ኢያሱም ያደፈ ልብስ ለብሶ ነበር

በዚህ ራዕይ ‘ያደፉ ልብሶች’ የኃጢአተኛነት ተምሳሌት ናቸው፡፡ (ተምሳሌታዊ ቋንቋ የሚለውን ይመልከቱ)