am_tn/zec/02/10.md

2.2 KiB

የጽዮን ልጅ ሆይ፣ እልል በዪ

‘ጽዮን’ የሚለው ‘ከኢየሩሳሌም’ ጋር አንድ ነው፡፡ ነቢዩ ስለ ከተማይቱ ሴት ልጅ እንደሆነች አድርጎ ይናገራል፡፡ ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፡ - 1) ዘካርያስ ከተማይቱን መዘመር በሚችል ሰው በሰውኛ ይገልጻታል፡፡ ትኩ. “ጽዮን፣ እልል በዪ” ወይም 2) ‘የጽዮን ልጅ’ በከተማይቱ ለሚኖሩ ሕዝቦች ስመ-ምስል ስያሜ ነው፡፡ ትኩ. “የጽዮን ሕዝቦች፣ እልል በሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ፣ ሰውኛ እና ስመ-ምስል ስያሜ የሚሉትን ይመልከቱ)

እኔ ራሴ ልመጣና በመካከላችሁ ልሰፍር ነው

“እኔ ራሴ ልመጣና በመካከላችሁ ልኖር ነው” ‘መስፈር’ ማለት ድንኳን መትከልና በድንኳኑ ተጠቅሞ መኖር ማለት ነው፡፡

ያህዌ … እንዲህ ይላል

እያወጀ ያለውን ነገር እርግጠኛነት ለመግለጽ ያህዌ ስለ ራሱ ስሙን በመጥቀስ ይናገራል፡፡ በዘካርያስ 1፡4 ላይ ተመሳሳይ የሆነውን ሐረግ እንዴት እንደተረጎማችሁት ዞር ብላችሁ ተመልከቱ፡፡ አት. “የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንደዚህ ብሎ ተናግሯል” ወይም “እኔ የሠራዊት ጌታ ያህዌ የምናገረው ይህንን ነው” (‘መጀመሪያ፣ ሁለተኛ፣ ሶስተኛ ሰው’ የሚለውን ይመልከቱ)

ታላላቅ ሕዝቦች ወደ ያህዌ ይጠጋሉ

ዘካርያስ የታላላቅ መንግሥታት ሕዝቦች የያህዌ ሕዝቦች እንደሚሆኑና ራሳቸውን ወደ ያህዌ እንዳስጠጉ ሁሉ እርሱን እንደሚያመልኩት አድርጎ ይናገራል፡፡ አት. “የታላላቅ መንግሥታት ሕዝቦች የያህዌ ሕዝቦች ይሆናሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ስመ-ምስል ስያሜ የሚሉትን ይመልከቱ)

በዚያ ቀን

‘በዚያን ጊዜ’

በመካከልሽም እሰፍራለሁ

‘በመካከልሽም እኖራለሁ’