am_tn/zec/02/08.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዘካርያስ አሁን መናገር ይጀምራል፣ ደግሞም ኢየሩሳሌምን በዘረፏት መንግሥታት ላይ ይፈርድ ዘንድ ያህዌ እንዴት እንደላከው ይናገራል፡፡

በዘረፉአችሁ

በዘረፉአችሁ በሚለው በውስጠ-ታዋቂ ‘እናንተ’ የሚለው የሚያመለክተው ኢየሩሳሌምን ነው፡፡

የሚነካችሁ

‘መንካት’ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ለመጉዳት የታሰበን መንካት ነው፡፡ አት. “የሚጎዳችሁ ማንም ቢሆን” (ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ዓይን ብሌን

የዓይን ብሌን በጣም ስስ (ለጉዳት የተጋለጠ) ከሆኑት የዓይን ክፍሎች አንዱ ነው፡፡ ‘የዓይን ብሌን’ የሚለው ፈሊጣዊ አባባል እጅግ ዋጋ ያለውን ነገር ያመለክታል፡፡ እዚህ ላይ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ታላቅ እሴት ሰጥቷታል ማለት ነው፡፡ አት. “ለእግዚአብሔር እጅግ ታላቅ ዋጋ ያለው” (ፈሊጣዊ አባባል የሚለውን ይመልከቱ)

እጄን በእነርሱ ላይ አነሳለሁ

እጅን በአንድ ሌላ ሰው ላይ ማንሳት የጠላትነት አዝማሚያ ነው፡፡ እዚህ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን የሚጎዷትን ያጠቃል የሚል ተምሳሌታዊ ትርጉም አለው፡፡ አት. “እኔ ራሴ እዋጋቸዋለሁ” ወይም “እኔ ራሴ አጠቃቸዋለሁ” (ተምሳሌታዊ ተግባር የሚለውን ይመልከቱ)

ለባሪያዎቻቸው ዝርፊያዎች ይሆናሉ

‘ዝርፊያ’ የሚለው ቃል በግሥ መልኩ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ትኩ. “ባሪያዎቻቸው ይዘርፏቸዋል”