am_tn/zec/02/03.md

3.7 KiB

ሌላ መልአክ ሊገናኘው መጣ

ይህ መልአክ ከዚህ በፊት ያልተከሰተ አዲስ ተሳታፊ ነው፡፡ (ቀደም ያሉና አዲስ ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ይመልከቱ)

ሁለተኛውም መልአክ እንደዚህ አለው

ሁለተኛውም መልአክ እኔን ሲያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ እንደዚህ አለው፡፡

ኢየሩሳሌም በገላጣ ስፍራ ትቀመጣለች … አውሬዎችም በውስጥዋ

‘በገላጣ ስፍራ ትቀመጣለች’ የሚለው ሐረግ ቅጠር የሌላትን ከተማ ለሚገልጸው ቃል ትርጉም ሆኖ ያገለግላል፡፡ በከተማይቱ እጅግ ብዙ ሰዎች ስለሚኖሩ በዙሪያዋ ቅጥር መሥራት እስከማይቻል ድረስ በጣም ሰፊ ትሆናለች፡፡ አት. “ኢየሩሳሌም በዙሪያዋ ቅጥር አይኖራትም … አውሬዎችም በውስጥዋ …” (ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

እኔ ለእርሷ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ

ሰዎች ለጥበቃ ዓላማ በከተሞቻቸው ዙሪያ ቅጥር ይገነባሉ፡፡ እዚህ ላይ ያህዌ እርሱ ራሱ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እንደሆነላት ሁሉ ኢየሩሳሌምን እንደሚጠብቃት ነው የሚናገረው፡፡ አት. “የእሳት ቅጥር በዙሪያዋ እንደሚሆንላት እኔ ኢየሩሳሌምን እጠብቃታለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ያህዌ … እንዲህ ይላል

እያወጀ ያለውን ነገር እርግጠኛነት ለመግለጽ ያህዌ ስለ ራሱ ስሙን በመጥቀስ ይናገራል፡፡ በዘካርያስ 1፡4 ላይ ተመሳሳይ የሆነውን ሐረግ እንዴት እንደተረጎማችሁት ዞር ብላችሁ ተመልከቱ፡፡ አት. “የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንደዚህ ብሎ ተናግሯል” ወይም “እኔ የሠራዊት ጌታ ያህዌ የምናገረው ይህንን ነው” (‘መጀመሪያ፣ ሁለተኛ፣ ሶስተኛ ሰው’ የሚለውን ይመልከቱ)

ዘካርያስ 2፡6-7 የትርጉም ማስታወሻዎች ኑ፣ ኑ

እነዚህ ሁለት ቃላት ጥድፊያን ያመለክታሉ፣ ለሚከተለውም ትዕዛዝ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ ቃላቱ በቋንቋችሁ ጥድፊያን በሚያመለክት ሐረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት. “ሩጡ፣ ሩጡ” ወይም “ቶሎ በሉ፣ ቶሎ በሉ” (ጣምራ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰሜን ምድር

ይህ የሚያመለክተው ባቢሎንን ነው፡፡

እንደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁ

‘አራቱ የሰማይ ነፋሳት’ የሚለው ሐረግ ‘በሁሉም አቅጣጫ’ ማለት ነው፡፡ ያህዌ ሕዝቡ በብዙ የተለያዩ አገሮች እንዲኖሩ ማድረጉን ነፍስ ከማንኛውም አቅጣጫ መንፈስ ከሚችልበት መንገደ ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ አት. “በየአቅጣጫው በትኛችኋለሁ፡፡ (ንፅፅሮሽ የሚለውን ይመልከቱ)

ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ

‘ባቢሎን ሴት ልጅ’ የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው የባቢሎንን ከተማ ነው፡፡ ያህዌ ስለ ከተማዋ ሴት ልጅ እንደሆነች አድርጎ እየተናገረ ነው፡፡ አት. “እናንተ በባቢሎች የምትኖሩ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)