am_tn/zec/01/20.md

2.3 KiB

አራት ሙያተኞች

‘የብረት አንጥረኞች’ ወይም ‘የብረት-ሥራ ሠራተኞች’

እነዚህ ሰዎች

ይህ የሚያመለክተው አራቱን ሙያተኞች ነው፡፡

እነዚህ ይሁዳን የበታተኑ ቀንዶች ናቸው

እነዚህ ቀንዶች የእስራኤልን መንግሥት ድል ያደረጉትን ኃይለኛ መንግሥታት በተምሳሌትነት ያመለክታሉ፡፡ ‘ይሁዳ’ የሚለው ቃል በይሁዳ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላል፡፡ በዘካርያስ 1፡19 ላይ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነውን ሐረግ እንዴት እንደተረጎማችሁት ዞር ብላችሁ ተመልከቱ፡፡ አት. “እነዚህ ቀንዶች የይሁዳን ሕዝብ የበታተኑትን መንግሥታት ይወክላሉ፡፡” (ተምሳሌታዊ ቋንቋ እና ስመ-ምስል ስያሜ የሚሉትን ይመልከቱ)

ማንም ራሱን ቀና ማድረግ እንዳይችል

የይሁዳን ሕዝብ በአሰከፊ ሁኔታ ሲጨቁኑ የነበሩት መንግሥታት ማንም ሰው ራሱን ቀና ማድረግ እንዳይችል እንዳደረጉ ተነግሮላቸዋል፡፡ አት. “በጣም እንዲሰቃዩ አደረጓቸው፡፡” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በይሁዳ ምድር ላይ ቀንዳቸውን መንግሥታት ቀንዶች ሰብሮ ለመጣል ነው

ወታደራዊ ኃይላቸውን በመጠቀም ይሁዳን ድል ለማድረግ የተነሱትን መንግሥታት ያህዌ መንግሥታቱ ቀንዳቸውን እንዳነሱ አድርጎ እየተናገረ ነው፡፡ የእነዚህን መንግሥታት ወታደራዊ ኃይል ሲደመስሱ የነበሩት አራቱ ሙያተኞች የመንግሥታቱን ቀንድ ሰብረው ወደ መሬት እንደጣሉ አድርጎ እየተናገረ ነው፡፡ አት. “በይሁዳ ምድር ላይ ወታደራዊ ኃይላቸውን የተጠቀሙትን የመንግሥታቱን ኃይል ለመደምሰስ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀንድ ያነሱትን የመንግሥታቱን ቀንዶች ለመስበር

“መንግሥታቱ ያነሷቸውን ቀንዶች ለመስበር”