am_tn/zec/01/16.md

3.9 KiB

በምሕረት ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሻለሁ

ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፡- 1)ምንም እንኳን ሕዝቡ ወደ ምርኮ በሄዱበት ጊዜ ያህዌ ኢየሩሳሌምን የተዋት ቢሆንም፣ አሁን ግን ሕዝቡ ከምርኮ በተመለሱ ጊዜ እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳል ወይም 2) ያህዌ ወደ ከተማይቱ እንደገና እየተመለሰ በሚመስል ሁኔታ ለኢየሩሳሌም በነበረው አመለካከት ላይ ለውጥ እንዳደረገና እንደገና እንደሚባርካቸው እንደሚረዳቸውም እየተናገረ ነው፡፡ አት. “ለኢየሩሳሌም እንደገና ምሕረቴን አሳያለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤቴ በውስጥዋ ይሠራል

‘በውስጥዋ’ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢየሩሳሌምን ሲሆን ‘ቤቴ’ የሚለው ደግሞ ለቤተ መቅደሱ ስመ-ምስል ስያሜ ነው፡፡ ይህ በተናጋሪ አነጋገር መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት. “ሕዝቡ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደሴን ይገነባሉ” (ስመ-ምስል ስያሜ እና ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚሉትን ይመልከቱ)

ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ አዋጅ ነው

እያወጀ ያለውን ነገር እርግጠኛነት ለመግለጽ ያህዌ ስለ ራሱ ስሙን በመጥቀስ ይናገራል፡፡ በዘካርያስ 1፡3 ላይ ተመሳሳይ የሆነውን ሐረግ እንዴት እንደተረጎማችሁት ዞር ብላችሁ ተመልከቱ፡፡ አት. “የሠራዊት ጌታ ያህዌ ያወጀው ይህንን ነው” ወይም “እኔ የሠራዊት ጌታ ያህዌ ያወጅሁት ይህንን ነው” (መጀመሪያ፣ ሁለተኛ፣ ሶስተኛ ሰው የሚሉትን ይመልከቱ)

መለኪያ ገመድም በኢየሩሳሌም ላይ ይዘረጋል

ይህ የሚያመለክተው ገንቢዎች ከተማይቱን እንደገና ለመገንባት መሣሪያዎቻቸውን እንደሚጠቀሙ ነው፡፡ ይህ በአናጋሪ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት. “ገንቢዎች የመለኪያ ገመዳቸውን በኢየሩሳሌም ላይ ይዘረጋሉ” ወይም “ሕዝቡ ኢየሩሳሌምን እንደገና ይገነባሉ” (ግምታዊ እውቀት፣ ውስጠ-ታዋቂ መረጃ እና ተናጋሪ ወይም አናጋሪ የሚሉትን ይመልከቱ)

በድጋሚ ተጣራና እንደዚህ በል

እነዚህን ቃላት የተናገረው ዘካርያስን ሲያነጋግር የነበረው መልአክ ነው፡፡

ከተሞቼ እንደገና በበጎነት ይትረፈረፋሉ

‘ከተሞቼ’ የሚለው የሚያመለክተው የይሁዳን ከተሞች ሲሆን በእነዚያ ከተሞች የሚኖሩትንም ሕዝቦች ይወክላል፡፡ በውሃ መያዣ በርሜል የተመሰሉትን እነዚያን ከተሞች፣ በጎነት የሚያጥለቀልቅ ውሃ እንደሆነ ሁሉ የእነዚያን ከተሞች ነዋሪዎች በበጎነት እንደሚያጥለቀልቃቸውና እንደገና ባለጠጎች እንዲሆኑ እንደሚያደርጋቸው ያህዌ ይናገራል፡፡ አት. “ከተሞቼ እንደገና ባለጠጎች ይሆናሉ” ወይም “በይሁዳ ከተሞች ያሉት ሕዝቦች እንደገና ባለጠጎች ይሆናሉ” (ስመ-ምስል ስያሜ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ያህዌ ጽዮንን እንደገና ያጽናናል

እዚህ ላይ ‘ጽዮን’ የሚለው ቃል የሚያመለክተው በከተማ የሚኖሩትን ሰዎች ነው፡፡ አት. “ያህዌ በጽዮን የሚኖረውን ሕዝብ እንደገና ያጽናናል” (ስመ-ምስል ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)