am_tn/zec/01/14.md

1.3 KiB

ለኢየሩሳሌም ቀንቻለሁ

እዚህ ላይ ‘ቀንቻለሁ’ የሚለው እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመጠበቅ የነበረውን ጠንካራ ፍላጎት ያመለክታል፡፡

ሰላም አለ በሚሉ ሕዝቦች ላይ ግን በጣም ተቆጥቻለሁ

‘ሰላም አለ’ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሕዝቡ በሰላምና በዕርጋታ እንደሚኖሩ እያሰቡ መሆኑን ነው፡፡ አት. “ሰላማቸውንና ደህንነታቸውን እያጣጣሙ ባሉት ሕዝቦች በጣም ተቆጥቻለሁ” (‘ፈሊጣዊ አነጋገር’ የሚለውን ይመልከቱ)

በመጠኑ ብቻ ተቆጥቼባቸው ነበር

“በኢየሩሳሌም ሕዝብ ላይ የተቆጣሁት በመጠኑ ብቻ ነበር”

ጥፋቱ እንዲብስ አደረጉ

“ሰላም አለ የሚሉት” ሕዝቦች ጥፋቱ እንዲብስ አደረጉ፡፡ ይህ ማለት ምንም እንኳን ያህዌ ኢየሩሳሌምን ለመቅጣት እነዚህን ሕዝቦች ቢጠቀምባቸውም እነርሱ ግን ያህዌ እነርሱ እንዲያደርጉ ካቀደው በላይ በኢየሩሳሌም ላይ ጉዳት አደረሱ ማለት ነው፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)