am_tn/zec/01/10.md

1.8 KiB

በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ የነበረው ሰው … በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ የነበረው የያህዌ መልአክ

እነዚህ ሐረጎች የሚያመለክቱት በዘካርያስ 1፡8 ላይ ‘በአምባላይ (ቀይ) ፈረስ ላይ ተቀምጦ’ የነበረውን ሰው ነው፡፡ ትኩ. “በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ የነበረው ሰው … በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ የነበረው የያህዌ መልአክ” (‘ፈሊጣዊ አነጋገር’ የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ እነዚያ ናቸው … መለሱም … እንደዚህም አሉ

‘እነዚህ’ እና ‘እነርሱ’ የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት በባርሰነት ዛፎች መካከል ከነበረው ሰው ጀርባ የነበሩትን መጋላ (ቀይ)፣ ሐመር (የቀይ ዳማ) እና አምባላይ (ነጭ) ፈረሶችን ነው፡፡ ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፡- 1) በውስጠ-ታዋቂነት በፈረሶቹ ላይ የሚቀመጡ ሌሎች ሰዎች አሉ፣ እነዚህ ቃላትም የሚያመለክቱት እነዚያን በፈረሶቹ ላይ የሚቀመጡትን ነው፡፡ 2) ፈረሶቹ መነጋገር እንደሚችሉ ተደርገው የሰውኛ ገጽታ ተሰጥቷቸዋል፡፡ (ግምታዊ እውቀት፣ ውስጠ-ታዋቂ መረጃ እና ሰውኛ የሚሉትን ይመልከቱ)

በምድር ሁሉ መመላለስ

እየተመላለሱ ምድርን እንዲቃኙ ያህዌ እነዚህን መላኩ ውስጠ-ታዋቂ ነው፡፡ ይህ የባዘኑ ወይም የጠፉ መሆናቸውን አያመለክትም፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ውስጠ-ታዋቂ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)