am_tn/zec/01/07.md

2.7 KiB

በሁለተኛው ዓመት፣ ሳባጥ በሚባለው በዐሥራ አንደኛው ወር በሃያ አራተኛው ቀን

‘ሳባጥ’ የሚባለው በዕብራውያን ዘመን አቆጣጠር አሥራ አንደኛው ወር ነው፡፡ ሃያ አራተኛው ቀን በአውሮፓውያን (ግሪጎርያን) አቆጣጠር በየካቲት ወር አጋማሽ ላይ የሚውል ነው፡፡ (የዕብራውያን ወሮች፣ መደበኛ ቁጥሮች እና ስሞችን እንዴት መተርጎም እንደሚገባ የሚሉትን ይመልከቱ)

ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት

“የንጉሥ ዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ሁለተኛው ዓመት” ወይም “ንጉሥ ዳርዮስ ንጉሥ ከሆነ በኋላ በሁለተኛው ዓመት” በዘካርያስ 1፡1 ላይ ይህንን እንዴት እንደተረጎማችሁት ዞር ብላችሁ ተመልከቱ፡፡ (‘መደበኛ ቁጥሮች’ የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል መጣ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ጥቅም ላይ የሚውለው ከእግዚአብሔር የመጣን የተለየ መልእክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ በዘካርያስ 1፡1 ላይ ይህንን እንዴት እንደተረጎማችሁት ዞር ብላችሁ ተመልከቱ፡፡ አት. “እግዚአብሔር መልእክት ሰጠ (አስተላለፈ)” ወይም “ያህዌ ይህንን መልእክት ተናገረ” (‘ፈሊጣዊ አነጋገር’ የሚለውን ይመልከቱ)

በራክዮ … አዶ

እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡ (‘ስሞችን እንዴት መተረጎም እንደሚገባ’ የሚለውን ይመልከቱ)

ተመለከትሁ

እዚህ ላይ ‘መመልከት’ የሚለው ቃል ዘካርያስ ባየው ነገር እንደተደነቀ ያመለክታል፡፡

ባርሰነት ዛፎች

ደማቅ አበቦች ያሉት አነስተኛ የዛፍ ዓይነት ነው፡፡ (የማይታወቁትን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)

እኔም፣ “ጌታ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁ፡፡ ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም …

እዚህ ላይ ዘካርያስ ማንነቱ ያልተገለጸውን መልአክ እያነጋገረ ነው፡፡ ይህ ‘በመጋላ (ቀይ) ፈረስ ላይ ከተቀመጠው ሰው’ ጋር ተመሳሳይ አይደለም፡፡

ጌታ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው?

“ጌታው፣ እነዚህ ነገሮች ምንድን ናቸው?” እዚህ ላይ ‘ጌታ’ የሚለው የትሕትና አነጋገርን የሚያመለክት ነው፡፡