am_tn/zec/01/01.md

2.4 KiB

በስምንተኛው ወር

ይህ የዕብራይስጡ ስምንተኛው ወር ነው፡፡ በምዕራባውያኑ (ጎርጎሳውያኑ) የዘመን አቆጣጠር በጥቅምት ወር መጨረሻና በኅዳር ወር መጀመሪያ ግድም የሚውለው የዓመቱ ክፍል ነው፡፡ (‘የዕብራውያኑ ወራትና መደበኛ ቁጥሮች’ የሚለውን ይመልከቱ)

የዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ሁለተኛው ዓመት

“የንጉሥ ዳርዮስ ዘመነ መንግሥት ሁለተኛው ዓመት” ወይም “ንጉሥ ዳርዮስ ንጉሥ ከሆነ በኋላ በሁለተኛው ዓመት” (‘መደበኛ ቁጥሮች’ የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል መጣ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ጥቅም ላይ የሚውለው ከእግዚአብሔር የመጣን የተለየ መልእክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ትኩ. “እግዚአብሔር መልእክት ሰጠ (አስተላለፈ)” ወይም “ያህዌ ይህንን መልእክት ተናገረ” (‘ፈሊጣዊ አነጋገር’ የሚለውን ይመልከቱ)

ያህዌ

ይህ በብሉይ ኪዳን ለነበሩት ሕዝቡ የገለጠው የእግዚአብሔር ስም ነው፡፡ ይህን እንዴት መተርጎም እንደሚገባ በሚመለከት በትርጉም ቃል ገጽ ስለ ያሀዌ የተጠቀሰውን ይመልከቱ፡፡

በራክዮ … አዶ

እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡ (‘ስሞችን እንዴት መተረጎም እንደሚገባ’ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር በአባቶቻችሁ ላይ እጅግ ተቆጥቶ ነበር

“በቀደሙት አባቶቻችሁ ላይ በጣም ተቆጥቶ ነበር”

ወደ እኔ ተመለሱ … እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ

ለሚመለስ ወይም እንደገና ለሚመለስ አንድ ሌላ ሰው የአመለካከት ለውጥ እያደረገ እንደሆነ አድርጎ ያህዌ ይናገራል፡፡ ሕዝቡ ወደ ያህዌ ተመለሱ ማለት እንደገና ለእርሱ የተሰጡ ይሆናሉ እርሱንም ያመልኩታል ማለት ሲሆን ያህዌ ወደ ሕዝቡ ተመለሰ ማለት ደግሞ እንደገና ይባርካቸዋል፣ ይረዳቸዋልም ማለት ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)