am_tn/sng/08/14.md

1.0 KiB

የእኔ ተወዳጅ

ሐረጉ ሴቲቱ የምትወደውን ሰውዬ ያመለክታል። በአንዳንድ ቋንቋዎች “የእኔ አፍቃሪ” ማለቷ በይበልጥ የተለመደ ሊሆን ይችላል። መኃልይ 1፡13ን እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእኔ ውድ” ወይም “የእኔ አፍቃሪ”።

ሚዳቋ

ቀጭን፣ አጋዘን መሳይ ባለ ረጅም ጠምዛዛ ቀንድ እንስሳ

ወንድ አጋዘን

ጎልማሳ ወንድ አጋዘን

የቅመማ ቅመም ተራሮች

“ቅመማ ቅመም የሞላባቸው ተራሮች”። ሴቲቱ ይህንን ዘይቤአዊ አነጋገር ሰውየው ከእርሷ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንዲፈጽም ለመጋበዝ ትጠቀምበታለች። ሰውየው በመኃልይ 4፡8 የከርቤ ተራሮችንና የዕጣን ኮረብቶችን እንዴት በዘይበአዊ አነጋገር እንደገለጻቸው ተመልከት።