am_tn/sng/08/11.md

2.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡ 1) ሴቲቱ ፍቅሩን ለሚሰጣት ለሰውየው ራሷን የምትሰጥበትን መንገድ ሰለሞን የወይን ቦታውን ገንዘብ ለሚከፍሉት ሰዎች ከሚያከራይበት መንገድ ጋር ታነጻጽራለች። 2) ሰውየው ለሌላ ሰው የማይሰጣትን ሴቲቱን ሰለሞን ለሌሎች ሰዎች ከሚሰጣቸው የወይን ቦታ ጋር ያነጻጽራታል።

ብኤልላሞን

ይህ በእስራኤል ሰሜኑ ክፍል የሚገኝ ከተማ ስም ነው።

የወይን ቦታውን ሰጠ

ኮንትራት፤ ሌሎች ሰዎች እየከፈሉት ወይኖችን በወይን ቦታው እንዲያበቅሉ ተስማምቶ በኮንትራት አከራየው

ማስተዳደር ለሚችሉ

“ሊንከባከቡ ለሚችሉ ሰዎች”

እያንዳንዱ ለፍሬው አንድ ሺህ የብር ሰቅል ማምጣት ነበረበት

ይህ ክፍያ ለወይን ቦታው ፍሬ እንደሆነ መግለጽ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። አ.ት፡ “እያንዳንዱ ሰው ለወይኑ ቦታ ፍሬ አንዳንድ ሺህ ሰቅል ብር ለሰለሞን መስጠት ይጠበቅበታል”

አንድ ሺህ ሰቅል ብር ለማምጣት

“1000 ሰቅል የብር ለማምጣት”

የወይን ቦታዬ፣ የእኔ የራሴ

ሴቲቱ በመኃልይ 1፡6 እንዳለው ራሷን የወይን ቦታ አድርጋ ታመለክታለች። እዚህ ጋ ማንም ከእርሷ ውጪ ስለ ወይን ቦታው መወሰን እንደማይችል አጽንዖት ትሰጣለች።

በፊቴ ነው

ይህ አንድ ሰው ማድረግ ስለሚፈልገው ነገር የማድረግ መብት እንዳለው የሚገልፅ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በእኔ ኃላፊነት ስር ነው” ወይም “እንደ ፈለግሁ ማድረጉ የእኔ ፈንታ ነው”

ሺህ ሰቅሎች ላንተ ናቸው፣ ሰለሞን

ሴቲቱ ሰለሞን የወይን ቦታውን በኮንትራት በማከራየት ገንዘብ ማግኘት እንደቻለ ታውቃለች፤ ነገር ግን እርሷ ገንዘብ አትፈልግም።

ሰቅሎች

“ሳንቲሞች”

ሰለሞን

አንዳንድ ትርጉሞች ሴቲቱ የምትናገረው በቀጥታ ለሰለሞን እንደሆነ ይረዳሉ። ሌሎች የሚረዷት በምናቧ ለጓደኞቿ፣ ለሰውየው ወይም ለራሷ እንደምትናገር አድርገው ነው።

ሁለት መቶ ሰቅሎቹ

ተናጋሪው ካሁን በፊት ይህንን አልጠቀሰም ነበር ፤ አድማጭ ግን ሴቲቱ ሰዎቹ በወይን ቦታው ሠርተው ለሰለሞን ከከፈሉት በኋላ ለራሳቸው የሚቀራቸውን ገንዘብ እንደምታወራ ይረዳል።