am_tn/sng/08/07.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ወጣቷ ሴት ለሰውየው መናገሯን ትቀጥላለች።

የማዕበል ውኃ ፍቅርን ሊያጠፋ አይችልም

እጅግ እንደሚነድ፣ ውቅያኖስ ሙሉ ውሃ እንኳን ቢደፋበት እንደማይጠፋ እሳት፣ ፍቅር ኃይለኛ ነው።

የማእበል ውሃ

“የውቅያኖስ ውሃ” ወይም “ብዙ ውሃ”

ሊያጠፋው አይችልም

“ማጥፋት አይችልም” ወይም ”ሊያስወግደው አይችልም”

ጎርፍ ሊጠርገውም አይችልም

ኃይለኛ ጎርፍም እንኳን እስከማያንቀሳቅሰው ድረስ ፍቅር መቼም አይቀየርም፤ ሁሌም ጸንቶ ይኖራል።

ጎርፍ

በእስራኤል የዝናብ ውሃ ወደ ጠባብና ጥልቅ ሸለቆዎች ይወርዳል። ይህም ግዙፍ ቋጥኞችንና ዛፎችን ማንቀሳቀስ የሚያስችለውን ጎርፍ ይፈጥራል።

ጠርጎ ይወስደዋል

“ይዞት ይሄዳል” ወይም “ያጥበዋል”

ሰው ቢሰጥ … ያቀረበው ፈፅሞ ይናቃል

ይህ ሊያጋጥም የሚችል ነገር ነው። አ.ት፡ “ሰው ቢ … እንኳን ፈጽሞ ይናቃል”

ሰጠ

ለመስጠት አቀረበ

በቤቱ ያለውን ንብረት ሁሉ

“የእርሱ የሆነውን ነገር ሁሉ”

ስለ ፍቅር

“ፍቅርን ለማግኘት” ወይም “ፍቅርን ለመግዛት”

ያቀረበው ፈፅሞ ይናቃል

ይህ በገቢራዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች ፈጽመው ይንቁታል” ወይም “ሰዎች በማፌዝ ይስቁበታል”